አይጊሮስ

ከውክፔዲያ

አይጊሮስ (በፓውሳኒዩስአፍሪካኑስ ዘንድ፣ ግሪክ፦ Αίγυρος) ወይም አይጊድሮስ (በጀሮምአውሳብዮስ ዘንድ፣ ግሪክ Αίγυδρος) በሲክዮን ነገሥታት ዝርዝር የአርጊያሌያ (በኋላ ሲክዮን) ንጉሥ ነበር። ካስቶርን የጠቀሱት ጸሐፊዎች 34 ዓመት እንደ ነገሠ ይላሉ። ይህ ምናልባት 2191-2157 ዓክልበ. ግድም ያህል ነው። በዝርዝሩ ላይ ከጤልክሲዮን ቀጥሎና ከጡሪማቆስ በፊት ይገኛል። ፓውሳኒዩስም የጤልክሲዮን ልጅና የጡሪማቆስ አባት ይለዋል።

ቀዳሚው
ጤልክሲዮን
የአይጊያሌያ (ሲክዮን) ንጉሥ
2191-2157 ዓክልበ. ግድም (አፈ ታሪክ)
ተከታይ
ጡሪማቆስ