አይጦ

ከውክፔዲያ
አይጦ

አይጦ ወይም ማውስ የሚባለው የኮምፒውተር ክፍል ሲሆን በስክሪን ላይ መጠቆሚያውን ለመቆጣጠር ይረዳል። ይህንንም የሚያደርገው በታችኛው ጠፍጣፋ ገጹ በተዘጋጀለት ምንጣፍ ወይም ጠረንጴዛ ላይ በመንሸራተት ነው። በአካላዊ ይዘቱ በሰው እጅ በሚያዝ መልኩ የሚሰራ እና አንድ ወይም ከዚያ በላይ ቁልፎች ያሉት አካል ነው። አንዳንድ ጊዜ ተጨማሪ ስራዎችን ለማከናወን የሚያስችል የሚሽከረከር ቁልፍ ሊያካትት ይችላል።