አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

ከውክፔዲያ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲአዲስ አበባኢትዮጵያ የሚገኝ የመጀመሪያውና ትልቁ የመንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ነው። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ስምነት የኢትዮጵያን የትምህርት ፋናንና ዕርምጃን እንዲያሳይ ታኅሣሥ ፱ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ.ም. ከመመረቁ በፊት፣ መሠረቱ በንጉሠ ነገሥቱ ጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፵፪ ዓ.ም. ተጣለ። ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ አዲስ አበባ በመባል ይታወቅ ነበር፤ በኋላም የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ የሚል ስያሜ የነበረው ሲሆን የዘውዳዊው መንግሥት ሥርዓት ካከተመ በኋላ የተመሠረተው ወታደራዊ መንግሥት አሁን በሚጠራበት ስሙ ሰይሞታል።


አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋና አስተዳደሩን ሰድስት ኪሎ በሚገኘው በዋናው ግቢ ያደረገ ሲሆን በአምስት ኪሎ (የቴክኖሎጂ ፋኩለቲ-ሰሜን)፣ በአራት ኪሎ የሳይንስ ፋኩልቲ፣ በስድስት ኪሎ (የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋኩልቲ እንዲሁም የኢንፎርማቲክስ ፋኩልቲ)፣ በጥቁር አንበሳ (የህክምና ፋኩልቲ ) በልደታ (የቴክኖሎጂ ፋኩለቲ-ደቡብ)፣ በብሔራዊ (የአዲስ አበባ ንግድ ስራ ኮሌጅ)፣ በሚኒሊክ (የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት)፣ የጥርስ ህክምና ትምህርት ቤት፣ እንዲሁም በደብረዘይት ከተማ የእንሰሳት ህክምና ፋኩልቲን ያስተዳድራል። አዲስ አበባ በስሩ የሚከተሉትን ፋኩልቲዎች እና ኢንስቲቲዩቶች ይዟል፦

የማሕበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋኩልቲ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የኢንፎርማቲክስ ፋኩልቲ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የኢንፎርማቲክስ ፋኩልቲ በአዲስ መልክ የተመሠረተው በ1994 ዓ.ም. ሲሆን ቀድሞ ሲሳ (ስኩል ኦፍ ኢንፎርሜሽን ስተዲስ ፎር አፍሪካ) በመባል ይታወቅ ነበር። በአሁኑ ሰዓት የኢንፎርማቲክስ ፋኩልቲ በስሩ የኢንፎርሜሽን ሳይንስ ትምህርት ክፍልን እና የኮምፒዩተር ሳይንስ ትምርት ክፍልን ይዞአል። ሁለቱም የትምህርት ክፍሎች የባችለርና የማስተርስ ፕሮግራሞች አሉዋቸው።

ኢንፎርሜሽን ሳይንስ ማለት ኢንፎርሜሽን ሳይንስ ማለት ነው?

የሕክምና ፋኩልቲ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የቴክኖሎጂ ፋኩለቲ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የሳይንስ ፋኩልቲ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የትምህርት አስተዳደር ፋኩልቲ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የድህረ ምረቃ ት/ት ክፍል[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የእንሰሳት ህክምና ፋኩልቲ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሌሎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የውጭ መያያዣ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]