አገውኛ
አገውኛ በኢትዮጵያና በኤርትራ የሚነገር ኩሺቲክ ተብሎ በሚታወቀው የቋንቋ መደብ የአፍሮ-እስያ ቤተሰብ የሚካለል ቋንቋ ነው።
የአገው ሕዝብ አኹን በሚኖርባቸው አካባቢዎች ራሱን የሚገልጸው አዊ ፡ኽምራ፡ቅማንት ፡ብሊን በሚሉ አካባቢያዊ መጠሪያዎች ነው !
የስያሜው እድገት ከራሳቸው ወይም በጋራ ከሚገኝ ማህበረሰብ ክፍሎች ተጨማሪ ቋንቋ የተዋሱት ነው
✓አዊ ማለት አገው ማለት ነው ፡የቃሉ መነሻና ምንጭ የራሱ ቋንቋ አገውኛ ነው ሌሎችንም ራሱንም አገው ለማለት ና ለመግለጽ ይህንኑ ቃል ይጠቀማል።
✓ ኽምራ ማለት አገው ማለት ነው የቃሉ መነሻና ምንጭ የራሱ ቋንቋ አገውኛ ነው ፡ሌሎቹንም ራሱንም አገው ለማለት ይኸንኑ ቃል ይጠቀማል።
✓ቅማንት ማለት የአማራ ልጅ ሲሆን እምነቱ ደግሞ ቅማንት ነው የቤተሰብ ውቅር አሰያየም ወይም የባህላዊ ሃይማኖት ማኅበረሰባዊ ልየታ ሲኾን የቃሉ መነሻና ምንጭ ዐማርኛ ነው ፡ ቃሉን የሚጠቀሙት የኦርቶዶክስ ክርስትያን ተከታዬች ሲሆኑ ክርስትናም ይሁን ይሁዲ እምነት የማይከተሉትን ቀደምት አገዎችን ክርስትያን አማሮች የሚገልጹበት ስያሜ ነው ።
✓ብሊን ማለት አገው ማለት ነው ፡የቃሉ መነሻና ምንጭ የራሱ አገውኛ ቋንቋ፡የቤላ ትውፊትና በጋራ ካሉት የሳሆ ቋንቋ ተናጋሪዎች የተወሰደ ሲሆን አገዎች ራሳቸውንና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ደግሞ አገዎችን ለመግለጽ ይጠቀሙበታል።
| ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |