Jump to content

አገው ምድር

ከውክፔዲያ

አገው ምድር (አዊ ላጜታ) በሀገሪቱ ስርዓት አዊ ብሄ/አሰ/ዞን እየተባለ የሚጠራው አካባቢ ሰው ያልነበረበት ፣ጥቅጥቅ ያለ ጫካ በዱር አራዊት የተሞላ ፣ ንፁህ የአየር ንብረት ለም አፈር ፣በቂ ውሃ ምቹ መልካአ ምድራዊ አቀማመጥ፣ የጫካ ማር ያለበት ጠፍ እንደነበረ አፋአዊ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡ ይሁን እንጂ የዚህ ቦታ ስያሜ የተሠጠው በአካባቢው በቀዳሚነት በሰፈሩት ሰባቱ አገው ወንድማማቾች መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ አገው ምድር እየተባለ የሚጠራው ቦታ በመጀመሪያዎቹ ነዋሪዎች ሲሰየም ክልሉ (ወስኑ እስከ የት እንደነበር በትክክል መግለፅ ባይቻልም ከአሁኑ አዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ስር ካሉ ወረዳዎች በላይ እንደነበር እንዲሁም በምስራቅ ጎጃምና ደ/ጎንደር አካባቢ በአዊኛ ቋንቋ የሚጠሩ አካባቢዎች (ቦታዎች )መኖራቸው ለብሄ/አስ/ዞን ወስንና ስፋት ዋነኛ እማኞች ለምሳሌ፡- ድኩል ካን ፣ዳድ ዩሃንስ (ምስ/ጎጃም ) ቢዝራ ካኒ (ጎንደር) ፃና (ጣና) የሚባሉት ተጠቃሽ ናቸው ሰባት ቤት አገው (ላጜታ አዊ) የተጠናከረና የተደራጀ መረጀ ባይኖርም በአፈ ታሪክ ደረጃ ከተለያዩ አባቶችና ታሪክ አዋቂዎች የተገኙ መረጃዎች (oral sources) እንደሚጠቁመን የእስራኤል ደም ወገን የሆነው ንጉስ ሰለሞን የልጅ ኩሳ ከቀዳማዊ ሚኒሊክ ጋር ታቦተ ፅዮንን ከእየሩሳሌም ይዘው ከመጡ በኋላ ንጉስ ኩሳ ሰቆጣ አካባቢ ትዳር መስርቶ በመኖር አዲልን ወለዱ ፣አዲል ደግሞ እና አንከሻ፣ባጃ፣መተከል፣አዘ ና፣ዚገም፣ኳኩራና ጫራን ወለዱ እነዚህ ወንድማማቾች ከአካባቢያቸው ወደ ተለያዩ ቦታ እየተዘዋወሩ ዱር አራዊትን በማደን አዘውትረው ሲኖሩ ኑሮን ለማሸነፍ ፣ህይወትን በተሻለ መንገድ ለመምራት ከተፈጥሮና አካባቢ ጋር መታገል ግድ ይላል ፡፡ ካልሆነም አካባቢን ለቆ የተሻለ አካባቢ ፍለጋ መኳተን አሁንም በአንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋል ተግባር ነው ፡፡ ስለሆነም ስባቱ አገዎች በአንድ ተሰማርተው በወቅቱ ውድና ተፈላጊ የሆኑ የዱር አራዊት ማለትም የዝሆን ጥርስ ፣ጥርኝ ፣ዝባድና የመሳሰሉትን ፍለጋ ሲጓዙ የትውልድ ቦታቸውን ስቆጣ ለቀው አሁን እንጅባራ እየተባለ ወደ ሚጠራው አካባቢ (ከሰንግ ይባል )ነበር ደርሰው አሁንም በአዊኛ “አንጉች ካና” ይባላል ፡፡ አካባቢው ምንም ሰው የሌለበት ፣በቂ የሆነ የዱር አራዊትና ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ፣የዱር ማር ያለበት ፣ምቹ መልካዓ ምድራዊ አቀማመጥና ሰላም የሰፈነበት ቦታ ሆኖ በማግኘታቸው በአካባው ሁኔታና ተፈጥሮአዊ አቀማመጥ በመማረክ ለሰባት ወራት ያህል የዱር አራዊትን በማደን ቆይተው ሰባቱም ወንድማማቾች ወደ ቤተሰቦቻቸው (ሰቆጣ ) በመመለስ፣ለቤተሰቦቻቸውም ተመላልሰው ስለተመለከቱት አካባቢ መልካዓ ምድራዊ አቀማመጥ ፣ለኑሮ ምቹና ተስማሚ የአየር ንብረት ፣በውስጡ ያሉ የዱር አራዊትና ተፈጥሮአዊ ገፅታ ሲገልፁላቸው ቤተሰቦቻቸውም በሀሳባቸው ተስማምተው ለጥያቄአቸው አወንታዊ ምላሽ በመስጠት መልካም ፈቃዳቸውን መርቀው ልጡን ገመድ፣ባዳውን ዘመድ ያድርላችሁ ሲሉ ሰባቱ ወንድማማቾች ሚስቶቻቸውን ልጆቻቸውን ከብቶቻቸውን እንዲሁም ከቤተሰቦቻቸው አገልጋያቸው ትሆን ዘንድ የተላከቸውን አዱክን ጨምረው ጎዞቸውን ወደ ተመለከቱት አካባቢ ቀጠሉ፡፡ ወደ አዲሱ አካባቢ ደርሰው በታላቃቸው አንከሻ መሪነት ቦታ ሲከፋፈሉ አንከሻና ባንጃ አማካኝ የሆነ ቦታ ሲይዙ ኳክራን በምስራቅ ፣ጫራን በምዕራብ፣ዚገም፣መተከልና አዘና በስተደቡብ እንዲቀመጡ አድርገዋል፡፡ አማካይ በሆነ አቅጣጫ አንከሻና ባንጃ በመሆን አዱክ ታገለግላቸው ነበር ፡፡ በተጨማሪም ለሌሎች ወንድማማቾች በመሆኑ እንደ መገናኛ ይጠቀሙበት ነበር ይላሉ የታሪክ አባቶች ፡፡ አዱክ ከሰባቱ ወንድማማቾች ጋር በአገልጋይነት ከሰቆጣ የተላከችው አዱክ ስትቅልባቸውና ስታገለግላቸው ኑራ አምስቱ በተልያዩ አቅጣጫ ቦታ ቦታቸውን ሲይዙ እሷ ግን በታላቃቸው አንከሻና ባንጃ መካከል በመሆን እንድትኖር ተደርጓል፡፡ በመሆኑም አገልጋያቸው አዱክ በዕድሜ እየገፋች ለስራ ጉልበቷ እየደከመ ሲሄድ እንደገና መጦር ግድ ሆነባት ፡፡ በሁለቱ ወንድማማቾች ትርዳና ትጦር ጀመር ይህም ሲሆን አንከሻ በደቡብ አብልቶ አጠጥቶ አጥቦና አልብሶ ድንበራቸው በሆነ ቦታ ላይ ፀሐይ ሲሞቅ ብርዱም ሲለቅ አስቀምጦ ሲሄድ ፣ባንጃም በተራው በመውሰድ ቤቱ አሰንብቶ ለተረኛው ሲሰጥ እንደቤቱ አብልቶና አጠጥቶ በጥዋቱ ፀሐይ ሰትታይ ከቦተዉ የደርሣት ነበር በመሆኑም አዱክ በጥዋቱ ቁርና በቀጥር ሙቀት ይፈራረቀባት ስለነበር አንከሻንና ባንጃን ትመርቃቸው ነበር ይላሉ አባቶች(አባሆይ ዘሩ አለሙ) አንከሻን /ክምምባ ኹ ክም አንካ እይምኽ /እስከ ማታ ብላ ባንጃን ስግላ ቻንቑዋ ስግላ አንካ ኹ /የማለዳ እንጀራ ብላ/ እማ አዱክ የተለያዩ መላምቶች “አዱክ” የሰባቱ አገው እናት ናት እየተባለ ሲወራ ይስተዋላል ፡፡ ስለሆነም ከተለያዩ አባቶች ታሪክ አዋቂዎችና የአካባቢ ነዋሪዎች የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው አዱክ የሰባቱ አገው ወንድማማቾች “ ወላጅ እናት ” አይደለችም ነገር ግን እነሱ ወደ ዚህ አካባቢ ሲመጡ ከቤተሰቦቻቸው የተላከች አገልጋያቸው (ሞግዚታቸው ናት ) የሰባቱ ወንድማማቾች እናት ማናት ? ሲባል አዱክ ይባላል ይህም የሆነበት ምክንያት 1. የብረሄረሰቡ ባህል ፣ ቋንቋና ወግ መሰረት በዕድሜ ትልቅ የሆነች እህት ፣አክስት ፣የእንጀራ እናት ወይም አሳዳጊ 2. በኢትዮጴያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስርዓት መሰረት የክርስትና እናት 3. በመኳንት ወይም መሳፍንት ቤተሰብ ቤት ውስጥ የምታገለግል ፣ሴት የልጅ ጠባቂ ፣ቀላቢ እና ተንከባካቢ እንደ ወላጅ እናት “እናት” ተብላ እንደምትጠራ ይታወቃል ፡፡ ስለሆነም አዱክ የሰባቱ አዊ እናታቸው ሳትሆን ቀላቢያቸውና አገልጋያቸው እንዲሁም የልጆቻቸው ሞግዚታቸው በመሆኗ እናት ተብላ ትጠራለች ፡፡ አዱክ በአንዳንድ አካባቢዎች እማ-አዱክ ተብሎ ስሟ ሲጠራ ይስተዋላል፡፡ ይህ የሆነው “እማ” የሚለው ቅፅል ስም በዕድሜ ትልቅ ለሆኑ ሴቶችና እናቶች የሚሰጥ የክብር ስም በመሆኑ አዱክ የሰባት አገዋች አገልጋያቸውና የልጆቻቸው ሞግዚትም ስለሆነች እማ አዱክ እየተባለች በክብር ስትጠራ፣(በማ/ሰቡ ባህል ፣ወግ፣ቋንቋ የእምነት ስርዓት መሰረት ፣ታላቆችን በስም ብቻ አይጠሩም ፣በአክብሮት፣በትህትናና በማዕረግ ስማቸው ይጠራሉ። የአዱክ መቃብር በኳሪ ጎኻና ቀበሌ ፣በተርዬ ታራረ ዙሪያው በጥድ ዛፍ የተከበበ ካችንቲ ተራራ (አለት በስተ ደቡብ ፣የእማ አዱክ መቃብር ስፍራ ይገኛል፡፡ ምክንያቱም የድንጋይ ቁልል ይታያል፡፡ የመቃብር ቦታ እዚህ ለመሆኑ የሚያመለክቱ መረጃዎች 1. እማ አዱክን አንከሻና ባንጃ ይጦሯት ስለነበረና ይህ ቦታ ደግሞ የሁለቱ ወሰን (ድንበር መሆኑ ) 2. አንከሻና ባንጃ በሚጦሯት ጊዜ የሚረካከቡበት ቦታ ስለነበር 3. ይህ ቦታ ለሰባቱም ወንድማማቾች አማካይ (መገናኛ) በመሆኑ በታላቆች ምክርና መሪነት መመሪያቸው 4. በወቅቱ በቅርብ ርቀት (አካባቢ ቤተ ቤተክርስቲያን አለመኖር ተጠቃሽ አፋዊ መረጃዎች ናቸው ፡፡ በሰሜን የባንጃ በአሁኑ ወረዳችን ፋግታ ለኮማ ፣በስተ ደቡብ የአንከሻ (በሁኑ ባንጃ ወረዳ ) ክልል ፣ከአ/ቅዳም ከተማ ወደ ኮሰበር በሚወስደው ------መንገድ ፣አሮጌ እንጅባራ ወይም በድሮ አጠራር ሰፈር ገቢያ እንዳደረስን ወደ ቀኝ በኩል በመታጠፍ ቀጥ ብለን ብንሄድ በግራና በቀኝ በጥድ ዛፍ የተከበበ ልዩና ማራኪ የሆነ ታሪካዊ ቦታን እናገኛለን፡፡ ይህ ቦታ - በቀደምት አዱክን አንከሻና ባንጃ የሚረካከቡበት ሲሆን - ዙሮ ዙሮ ቤት ፣ኑሮ ኑሮ ሞት እንዳሉ በኋላም የእማዱክ መቃብር ስፍራ ነው ፡፡ እዚህ ቦታ መሀል ለመሀል ሰፊ የሆነ ጎዳ/መንገድ ከአ/ቅዳም ና እንጅባራ ወደ ኳሪ ጎኻና የሚያደርስ ሲኖረው በዚህ መንገድ የሚያልፍ ማንኛውም ሰው እንደሌለው አካባቢ ምንገድ አቋርጦ አያልፍም / አይሄድም ልዩ የሆነ ባህላዊ ታሪካዊ ስርዓት ያለማንም መካሪነትና ትዕዛዝ ሲፈፀም/ሲከናወን ይታያል፡፡ ይኸውም መንገደኛው እማዱክ መቃርብ ሊደርስ የተወሰነ ርቀት ሲቀረው በቀኝ እጁ ድንጋይ ይዞ መጣል አያያዙም እንደ ማንኛውም ተራ ውርወራ ሳይሆን ልክ በቀኝ እጁ ይዞ በትክሻው ቀጥታ ቦታው ላይ ሲደርስ በቀኝ በኩል ካለው የድንጋይ ክምር ይጠለዋል ፡፡ በመቀጠልም እዚች ቦታ ላይ ቁጭ ብሎ ያርፋል ፡፡ ይህ የሚካሄደው ምን ጊዜ በቀኝ በኩል ባለው ስፍራ ነው ፡፡ ለምን ቢሉ - በቀኝ እጅ መያዛቸው ቀኝ እጅ ሁልጊዜም ገር ፣ቀናና መልካም ዕድልና ምኞች በመሆኑ - ከቦታው ሲደርሱ ማረፊያ መቀመጫቸው ከእናታቸው በረከት ለመሳትፍ - ድንጋይ መጣል እረም ማውጣት ለመቃብር መታሰቢያነት ይህም በማ/ሰብ ወግና ባህል መሰረት ሰው ሲሞት እልቅሶ ቦታ ላይ ሲደርሱ ፊት ይጠረጋል ፣ቁጭ ብለው መነሳት፣ለወደፊቱም ለነፍስ መልካም መመኘት የተለመደ ስርዓት ነው ፡፡ የተለያዩ የፅሑፍ መረጃዎችን አፋዊ መረጃዎችን በመጠቀም መረጃዎችን በመሰብስብ ፅሑፉን ማጠናከር ተችሏል ፡፡ ማጠቃለያ ወረዳችን ይህንና የመሳሰሉ ጥንታዊና ታሪካዊ ህዝብ ባለቤት ልዩ ልዩ ጥንታዊና ባህላዊ ቅርሶች መገኛ የተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ መስህብ ስፍራዎች ባለቤት መሆኑን መገለጫ ለሆነው ባህላችንና ቅርሶቻችን ትኩረት ሰጥተን መጠበቅ መንከባከብና ተጠብቀው ለትውልድ የሚተላለፉበትን መንገድ ማመቻቸት የሁላችንም የህሊና ግዴታ ሊሆን ይገባናል ፡፡

የአዊ (አገው ምድር) የፈረስ ጉግስ ባህል

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ከ 70 ዓመታት በላይ የሆነው የ ‹‹ አዊ የፈረስ ማህበር›› ባህሉን ጠብቆ በማቆየቱ በ ‹‹ ቅርስና ባህል ዘርፍ ›› ለዘንድሮው የ ‹ በጎ ሰው ሽልማት› ከተመረጡ ሶስት ዕጩዎች አንዱ ሁኗል፡፡ የፈረስ ጉግስ ባህሉ ዝም ብሎ ለመዝናኛ የሚሆን ብቻ አይደለም፡፡ የማህበራዊ ስነ - ሰብ አጥኝዎች በአግባቡ ባያጠኑትም ቅሉ፣ የራሱ ታሪካዊ አመጣጥ አለው፡፡ ከታሪካዊ እውነታዎች እና አሁን የፈረስ ጉግስ ከሚዘወተርባቸው ሁነቶች ተነስቶ ሶስት መላምቶችን መገመት ይቻላል፡፡ 1 ኛ ) አንደኛው ከመከረኛው ጦርነት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ መኪና፣ አውሮፕላን እና ዘመናዊ የጦር መሳሪያ በሌለበት ዘመን አብዛኛው የእርስ በርስም ሆነ ከውጭ ጠላት ጋር ይደረጉ የነበሩ ውጊያዎች የሚከወኑት በጦር እና ጎራዴ በሚደረግ የጨበጣ ውጊያ ነው፡፡ የጨበጣ ውጊያን በድል ለማጠናቀቅ ደግሞ ፈረስ ትልቅ አስተዋፅኦ ነበረው፡፡ የአድዋ ጦርነት በፈረስ አጋዥነት ለድል እንደበቃ ብዙ ማሳያዎች አሉ፡፡ ለ ‹‹ ባንዳ እርግማን ›› አፋችን የሾለውን ያህል ‹‹ ፈረሶችን ›› አመስግነናቸው አናውቅም፡፡ ለኢትዮጵያ ነፃነት ከ ‹‹ ባንዳዎች ›› እና ‹‹ከፈሪዎች›› ይልቅ ፈረስ የነበረው አስተዋፅኦ ታላቅ ነው፡፡ ፈረስ ለቀደሙ ነገስታት ባለውለታ፣ የህይወታቸው አለኝታ ነበር፡፡ ለዚህም ይመስላል ብዙ ነገስታት ከ አባታቸው ይልቅ የፈረሳቸው ስም ጎልቶ የሚወጣው፡፡ ለምሳሌ የአፄ ቴወድሮስን ብናነሳ፡ ‹‹ ታጠቅ ብሎ ፈረስ፣ ካሳ ብሎ ስም አርብ አርብ ይሸበራል፣ ኢየሩሳሌም ››…… ተብሎ ተገጥሞላቸዋል፡፡ ኮ / መንግስቱ ሐይለማሪያም ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ ያለውን እና ለኦጋዴን ጦርነት በአንድ ቀን 300 ሺ ሰራዊት ያሰለጠኑበትን የጦር ሰፈር በጀግናው በአፄ ቴወድሮስ ፈረስ ስም ‹‹ ታጠቅ ›› ብለው መሰየማቸው በድንገት የሆነ አይደለም፡፡ ብዙ ትችት የደረሰበት ቴወድሮስ ካሳሁን በ ‹ ጥቁር ሰው › አልበሙ ውስጥ ደ / አዝማች ባልቻ ሳፎን ‹‹ ባልቻ አባቱ ነፍሶ ›› ብሎ ማቀንቀኑ በስህተት ወይም ዜማ ለማሳመር ሳይሆን ይህን ሃቅ በመረዳት ይመስለኛል፡፡ 2 ኛ ) ከቤተክርስቲያን ክብረ በዓል ጋር በተያያዘ የፈረስ ጉግስ ከሚዘወተርባቸው በዓላት መካከል የ ‹‹ ጥምቀት በዓል ›› እና ‹‹ ዓመታዊ የንግስ በዓላት ›› ቀዳሚዎች ናቸው፡፡ እግር ጥሎት የጥምቀት በዓልን አገው ምድር ያከበረ፣ ከታቦቱ በረከት ባለፈ በፈረስ ጉግሱ ተዝናንቶ ይመለሳል፡፡ ትንሽ የሚሞክር ከሆነም የአንዱን ፈረስ ተቀብሎ ‹‹ አይሞሎ ›› ማለትን ማንም አይከለክለውም፡፡ ከንግስ በዓላት ጋር ተያይዞ የሚደረገው ጉግስ ለ ‹‹ ቅዱስ ታቦቱ ›› ክብር የሚደረግ ነው፡፡ ባለፈረሶች የራሳቸውን ዜማ እየዘመሩ ታቦቱን ዙሪያውን አጅበውት ይዞራሉ፡፡ ታቦቱ በሰላም ወደ መንበሩ ከመለሱ በኋላ ወደ ሜዳ ሄደው ፈረስ ጉግስ ይጫወታሉ፡፡ 3ኛ ) ከለቅሶ ጋር በተያያዘ ዘመናዊ የትራንፖርት አገልግሎት ባልነበረበት ዘመን፣ የሩቅ ዘመድ ወዳጅ ሲሞት ፈጥኖ ለመድረስ፣ ወዳጅ ዘንድ ሄዶ ‹ አይንን ለማበስ › ትልቅ አስተዋፅኦ ነበረው/ አሁንም አለው፡፡ በተለይ ሟች የጦር ዘማች ከሆነ በባህሉ መሰረት ‹‹ ትልቅ የፈረስ ሰልፍ›› ይደረግለታል፡፡ ለሌሎች በእግር ሰልፍ የሚደረገው ሙሾ፣ ቀረርቶ እና ፉከራና ለዘማች ግን ‹‹ በፈረስ ሰልፍ ›› ይደረግለታል፡፡ ለቅሶ ላይ ጉግስ ባይኖርም ‹‹ ስጋር›› ግን የተለመደ ነው፡፡ ይህ መጀመሪያ ላይ ካነሳነው ‹‹ የጦርነት አውድ ›› ጋረ በእጅጉ የተቆራኘ ነው፡፡ ይህ ደግሞ አንድ ነገር ያሳያል፡፡ አገው ምድር ውስጥም ሆነ በአጎራባች የጎጃም ግዛቶች ፈረስን እንደመሳሪያ ተጠቅመው ለነፃነት ይታገሉ የነበሩ ጀግኖች እንዳሉ ያሳያል፡፡ በዘመን ሂደት ስማቸው የተዘነጋ አንዳድ ሰዎችን ልጥቀስ፡ ‹‹ ራስ ቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም፣ ፊታውራሪ ባይህ፣ ቀኝ አዝማች ስሜነህ ( ለደርግ አልገዛም ብሎ ከደርግ ጋር እየተዋጋ ወደ ሱዳን የሸሸ ) ፣ ግራ አዝማች አበጋዝ፣ ፊታውራሪ ሙላት ( የደራሲና ፀሀፌ ተውኔት አያልነህ ሙላት አባት) የመሳሰሉት በከፊል ይጠቀሳሉ፡፡ ሲጠቃለል የዘንድሮውን ሽልማት ለ ‹‹ አዊ ፈረስ ማህበር›› ማበርከት ባህሉን ጠብቀው ላቆዩት ማበረታቻ፣ በፈረስ ጫንቃ ሁነው ሲዋጉ ለተሰው ጀግኖች መታሰቢያ፣ ደመ ነፍስ ባይኖራቸውም በዱር በገደሉ ለኢትዮጵያ ነፃነት ለተዋደቁ ፈረሶች ምስጋና ይሆናል፡፡

የአዊ ብሔረሰብ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር አካባቢዎች ለተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ክዋኔዎች ቀዳሚ ሚና የሚጫወተው ፈረስ ነው። ፈረስ እርሻ በማረስ የነዋሪዎችን ገቢ ያሳድጋል፣ በአካባቢው እንግዳ ከመጣ የሚታጀበው በፈረስ ነው፣ ዓመታዊ ኃይማኖታዊና ዓለማዊ በዓላት የሚደምቁት በፈረስ ነው፣ ሠርግና ለቅሶ በአዊ ያለፈረስ የማይከወኑ ማህበራዊ ጉዳዮች ናቸው። • ሜድ ኢን ቻይና- የሀገር ባህል አልባሳቶቻችን በየዓመቱ ጥር 23 የሚከበረው "የሰባት ቤት አገው ፈረሰኞች ማኅበር" ደግሞ የአዊ ብሔረሰብና ፈረስ ያላቸውን ዘመን ያስቆጠረ ቁርኝት የሚያንጸባርቅ ኩነት ነው። ማኅበሩ ታዲያ እንዲሁ "በማኅበር እናቋቁም" ምክክር የተመሰረተ አይደለም። ታሪካዊ ጅማሮውን 120 ዓመታትን ወደኋላ ተጉዞ ከአድዋ ጦርነት ይመዝዛል። አለቃ ጥላዬ የማኅበሩ ሊቀ መንበር ናቸው። እርሳቸው እንደሚሉት በ1888 ዓ.ም በተደረገው የአድዋ ጦርነት ኢትዮጵያዊያን አርበኞች ወደ አድዋ የተጓዙትም የተዋጉትም በፈረስ ነው። በሁለተኛው የጣሊያን ወረራም ወቅትም ፈረስ ተመሳሳይ የአርበኝነት ተጋድሎ ውስጥ ተሳትፎ፤ ከአምስት ዓመታት ፍልሚያ በኋላ ጣሊያንን ድል መንሳት ተችሏል። በዚህ ሂደት ታዲያ ፈረስ በብዛት ለጦርነቱ ከተሳተፈባቸው ስፍራዎች መካከል የአዊ አካባቢዎች አንዱ ነበር። ይህ በመሆኑም "የፈረስና የአርበኛ ውለታው ምን ይሁን" የሚል ሃሳብ ተነስቶ የአካባቢው አረጋዊያን ምክክር አድርገው "በአድዋ፤ በኋላ በነበረውም የአምስት ዓመት የአርበኝነት ዘመን አጥንታቸውን ለከሰከሱት አርበኞችና ፈረሶች እንዲሁም በድል ለተመለሱት መታሰቢያ ለማድረግ ሲባል ማኅበሩ በ1932 ዓ.ም በሃሳብ ደረጃ ተጠንስሶ በዓመቱ 1933 ዓ.ም በይፋ ተቋቋመ" ይላሉ አለቃ አሳዬ። የፈረስ ጉግስ በአካባቢው ለዓመታት የተለመደ ቢሆንም በኃይማኖታዊ በዓላት ላይ ወጣቶች ውድድር አድርገው ታዳሚውን ያስደምማሉ፤ በግልቢያ ችሎታቸው ጉልምስናቸውን ያሳያሉ እንጂ በተደራጀ መልኩ የሚደረግ ዓመታዊም ሆነ ወርሃዊ ውድድር እንዳልነበረው አለቃ ጥላዬ ይናገራሉ። በኦሮምኛና በትግርኛ አፋቸውን የፈቱ የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ባለውለታዎች የ75 ዓመቱ አዛውንት አለቃ አሳዬ ተሻለ ከታዳጊነት የእድሜ ዘመናቸው ጀምረው አብዛኛውን እድሜያቸውን በአገው ፈረሰኞች ማኅበር ውስጥ አሳልፈዋል። አባታቸው ግራዝማች ተሻለ የማኅበር ምስረታ ሃሳቡን በማመንጨትና ማህበሩን በማቋቋም ረገድ ስማቸው ከሚነሳ ጥቂት ሰዎች መካከል አንዱ መሆናቸውን ያስታውሳሉ። የፎቶው ባለመብት, AWI የምስሉ መግለጫ, የአዊ ፈረሰኞች በወቅቱ የአሁኑ አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ባንጃና አንከሻ የሚባሉ ሁለት ወረዳዎች ነበሩት። አርበኞች ጣሊያንን ካባረሩ በኋላ የፈረስንና የአርበኞችን ገድልና ውለታ ለመዘከር ከባንጃ ወረዳ 16 ሰው፤ ከአንከሻ ወረዳ 16 ሰው በድምሩ 32 ሰው ሆነው የሰባት ቤት አገው ፈረሰኞች ማህበርን በ1933 ዓ.ም መመስረቱን ይገልጻሉ። "በጊዜው በዓመት ሁለት ጊዜ እንዲከበር ተወስኖ የነበረ ሲሆን ሚያዚያ 23 እና ጥቅምት 23 ደግሞ በዓሉ የሚከበርባቸው ቀናት ነበሩ" በማለት አለቃ አሳዬ የሰባት ቤት አገው ፈረሰኞች ማኅበርን ታሪካዊ ዳራውን ይተነትናሉ። የኬንያ ዳኞችን አለባበስ የቀየረች ኢትዮጵያዊት ማኅበሩ በተቋቋመበት ወቅት የፈረስ ጉግስ በማድረግና የቅዱስ ጊዮርጊስን ማሕበር በመጠጣት እንደተጀመረ የሚናገሩት አለቃ አሳዬ፤ ማህበሩን ያቋቋሙትም ከባንጃ ወረዳ አለቃ መኮንን አለሙና ግራዝማች ንጉሤ፤ ከአንከሻ ወረዳ ደግሞ ቀኛዝማች ከበድ ንጉሤና ግራዝማች ተሻለ (የአለቃ አሳዬ አባት) መሆናቸውን ይናገራሉ። በበዓሉ የተመረጡ ሰጋር ፈረሶች በተለያዩ አልባሳት አሸብርቀው ይቀርባሉ። ፈረሶቹ ለበዓሉ ማድመቂያ ብቁ መሆናቸው በአካባቢው ሰዎች ተረጋግጦ የተሻሉት ብቻ ለበዓሉ ይጋበዛሉ። ከሁሉም አካባቢዎች የመጡ ልምድ ያላቸው ጋላቢዎች ደግሞ በጉግስ፣ ሽርጥና በሌሎች የውድድር ዓይነቶች እነዚህን ፈረሶች በመጋለብ፤ በታዳሚው ፊት ልክ በጦርነት ወቅት ፈረሶች እንደነበራቸው ሚና በማስመሰል ትርዒት ያሳያሉ፤ በውድድሩ አሸናፊ የሆኑትም ሽልማት እንደሚበረከትላቸው የማኅበሩ ሊቀመንበር አለቃ ጥላዬ ያስረዳሉ። የፎቶው ባለመብት, AWI የምስሉ መግለጫ, የአዊ ፈረሰኞች በዓሉ በዚህ ሁኔታ ለብዙ ዓመታት በዓመት ሁለት ጊዜ እየተካሄደ ከቀጠለ በኋላ፤ የማኅበሩ አባላት እየበዙ በመምጣታቸውና በዝግጅቱ ውበትም ብዙ ሰው እየተማረከ በመምጣቱ ሰፋ ባለ ዝግጅት በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ እንዲከበርና ቀኑም ጥር 23 እንዲሆን ተወስኖ በየዓመቱ በዚሁ ዕለት እየተከበረ እንደሚገኝ አለቃ ጥላዬ ለቢቢሲ በሰጡት መረጃ አረጋግጠዋል። የብስክሌት ጀልባ የሠራው ወጣት በታሪክ በዓሉ የተከበረባቸው ሦስቱም ቀናት በተለያዩ ወራት ቢሆንም '23' በመሆናቸው ግን ልዩነት የለም። ለዚህ ደግሞ አለቃ ጥላዬ ዋነኛ ምክንያት ብለው የሚያስቀምጡት፤ በአድዋ ጦርነት ወቅት የቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦት ወደ ቦታው ተጉዞ ነበር ስለሚባል፤ ቀኑ የተመረጠው የቅዱስ ጊዮርጊስን መታሰቢያ ዕለት ምክንያት በማድረግ ነው ይላሉ። በ32 አባላት የተጀመረው የፈረሰኞቹ ማኅበር ዘንድሮ በ80ኛ ዓመቱ የአባላት ብዛቱን 53 ሺህ 2 መቶ 21 ማድረሱን ሊቀ መንበሩ አለቃ ጥላዬ ተናግረዋል። የማኅበሩ አባል ለመሆን ጾታ የማይለይ ሲሆን በእድሜ በኩል ከ18 ዓመት በላይ መሆን እና በአካባቢው ማሕበረሰብ ዘንድ የተመሰከረላቸውና ምስጉን መሆን ብቻ ብቁ ያደርጋል። ከአባልነት የሚጠየቀው መዋጮም በዓመት 8 ብር ብቻ ነው ይላሉ አባላቱ። የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በዘጠኝ ወረዳዎችና በሦስት ከተማ አስተዳደሮች የተዋቀረ ነው። ሁሉም ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች "የሰባት ቤት አገው ፈረሰኞች ማኅበር" አባል መሆናቸውን የአዊ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ መለሰ አዳል ያስረዳሉ። • ጣልያን በተሸነፈችበት አድዋ ቆንስላዋን ለምን ከፈተች? በዓሉ በእነዚህ ወረዳዎች በየዓመቱ በየተራ ይዘጋጃል የሚሉት አቶ መለሰ ተረኛ የሆነ ወረዳ ለበዓሉ ታዳሚ ባህላዊ ምግቦችንና በዓሉ በሚከበርበት ወቅት ተሳታፊ የሚቀመጥበትና ተወዳዳሪዎች የሚጋልቡበት የመጫወቻ ሜዳንም ያዘጋጃል ብለዋል። ዛሬ እየተከናወነ ያለው 80ኛው የአገው ፈረሰኞች በዓልም በተለያዩ የብሔረሰቡ አካባቢዎች ሲካሔድ ቆይቶ የማጠቃለያ ፕሮግራሙ በ2 ሺህ ፈረሶች አማካኝነት በእንጅባራ ከተማ እየተከበረ መሆኑን ኃላፊው አስታውቀዋል። የአካባቢው ሕዝብ በዓሉን በጉጉት ይጠብቀዋል። በበዓሉ የሚታዩ ትርኢቶች ተመልካችን ያስደምማሉ። ፈረስ ጋላቢዎች በሺዎች ለሚቆጠሩ ታዳሚያን ችሎታቸውን ለማሳየት ብቸኛዋ ቀን ጥር 23 ናት። የፎቶው ባለመብት, AWI የምስሉ መግለጫ, የአዊ ፈረሰኞች አምና በውድድሩ የተሸነፈው ዘንድሮ ለማሸነፍ፣ አሸናፊው ደግሞ አሸናፊነቱን ለማስቀጠል የሚያደርገው ትንቅንቅ፤ ፈረሶች በኋለኛ ሁለቱ እግሮቻቸው ብቻ ቀጥ ብለው ሲቆሙ ማየት ታዳሚያን በዓሉን እንዲናፍቁ ከሚያደርጉ ትዕይንቶች መካከል አንዱ ነው። አለቃ አሳዬ አባታቸው በመሰረቱት የፈረስ ማኅበር ውስጥ ተወዳዳሪም የማህበሩ የበላይ ጠባቂም በመሆን ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ አሳልፈዋል። ዘንድሮም በ75 ዓመት የእድሜ ዘመናቸው፤ 80ኛ የማህበሩን በዓል ለማክበር እንጅባራ ተገኝተዋል። በ1962 ዓ.ም አለቃ አሳዬ መኖሪያቸውን ከአንከሻ ወደ ቻግኒ ቀይረዋል፤ በአዲሱ የመኖሪያ አድራሻቸውም ላለፉት 50 ዓመታት በበዓሉ ግንባር ቀደም ፈረስ ጋላቢ በመሆንና ማኅበሩን በማጠናከር የማይተካ አስተዋጽዖ ሲያበረክቱ ቆይተዋል። ሰክሮ በፈረስ ግልቢያ ውድድር ላይ የተሳተፈው ታሰረ እርሳቸው ከሚኖሩበት ቻግኒ ከተማ በዓሉ እስከሚከበርበት እንጅባራ ያለው ርቀት 60 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ ነው። ይህንንም ርቀት ፈረሳቸውን ጭነው ባለፉት 50 ዓመታት ሲጓዙት ኖረዋል። ዘንድሮም ዕድሜ ሳይገድባቸው ይህንን 60 ኪሎ ሜትር ርቀት በ4 ሰዓታት በሰጋር ፈረሳቸው ተጉዘው እንጅባራ ተገኝተዋል። "ሚሊዮን ብር ሰጥተው ከፈረስ ማኅበሩ በዓል እንድቀር አማራጭ ቢሰጠኝ ዝግጅቱ ላይ መገኘትን እመርጣለሁ" የሚሉት አንድም ቀን ከበዓሉ ተለይተው የማያውቁት አለቃ አሳዬ ዛሬም ለውድድር ባይሆንም ፈረስን እንዴት በቄንጥ መጋለብ እንደሚቻል በማሳየት ታዳሚን ጉድ ሊያስብሉ ተዘጋጅተዋል። • በአውስትራሊያ ፈረሶች እየታረዱ ነው በሚል ውንጀላ ላይ ምርመራ ተጀመረ በአሁኑ ወቅት የበዓሉ አድማስ ከአካባቢው ማህበረሰብ አልፎ በአገር አቀፍ ደረጃ ቦታ የሚሰጠው ሆኗል። በየዓመቱ በርካታ የአማራ ክልል ባለስልጣናትና ነዋሪዎች በዓሉን ለመታደም ወደ አካባቢው ይተማሉ። ከክልሉ ውጭ የሚገኙ ነዋሪዎችና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በበዓሉ ተማርከው ጥር 23ን በአገው ምድር እንጅባራ ማሳለፍን ምርጫቸው እያደረጉ ነው። በዘንድሮው በዓልም ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን፣ የባህልና ቱሪዝም ሚንስትሯ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር) እና ሌሎች በርካታ የፌደራልና የክልል ባለስልጣናትም የበዓሉ ተሳታፊዎች ናቸው።