አፍሮ እስያዊ ቋንቋዎች
Appearance
(ከአፍሮ ኤዥያዊ የተዛወረ)
አፍሮ እስያዊ ቋንቋዎች በሰሜን አፍሪቃና በደቡብ ምዕራብ እስያ የሚነገሩ ቋንቋዎች ቤተሰብ ሲሆን 6 ንዑሳውያን ቤተሰቦች አሉት።[1] እነዚህም ጥንታዊ ግብጽኛ፣ በርበርኛ፣ ቻዳዊ፣ ኩሻዊ (ሐማዊ)፣ ኦሞአዊና ሴማዊ ቋንቋዎች ናቸው።[1] ከእነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ውስጥ 3ቱ ማለትም ኩሻዊ (ሐማዊ)፣ ኦሞአዊና ሴማዊ ቋንቋዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ይነገራሉ።[1] በዕድሜ ረገድ ግዕዝና ግብጽኛ ጥንታዊ ቋንቋዎች ሲሆኑ፣ በኢትዮጵያ ታሪክ ኩሻዊና ኦሞአዊ መጀመርያ የገቡት፣ ሴማዊ ቋንቋዎች ከእነሱ ቀጥለው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ናቸው።[1]
- ^ ሀ ለ ሐ መ ዶ/ር አንበሴ ተፈራ፣ «የኢትዮጵያ ብሔረሰቦችና ቋንቋዎቻቸው አጭር ቅኝት Archived ጁን 17, 2012 at the Wayback Machine»