Jump to content

አፖሎ ፲፩

ከውክፔዲያ
የአፖሎ 11 አርማ

አፖሎ 11 ለመጀመሪያ ጊዜ ሰወችን ከመሬት ወደ ጨረቃ ለማጓጓዝ የተዘጋጀ የመንኮራኩር ሚስዮን ነው። ይህ ጉዞ የተቀናበረው በአሜሪካው የጠፈር አጥኝ ተቋም ናሳ ነበር። መንኮራኩሩ ሐምሌ16 1961ዓ.ም ከመሬት ሲመጥቅ፣ በውስጡ ሶስት ጠፈርተኞችን፣ ማለትም ኔል አርምስትሮንግበዝ አልድሪንማይክል ኮሊንስን የያዘ ነበር። መጓጓዣ መንኮራኩሩ ጨረቃ ላይ ከ4 ቀን በኋላ ሐምሌ 20 ሲደረስ፣ በዚሁ ቀን አርምስትሮንግና አልድሪን የጨረቃን ምድር በእግራቸው በመርገጥ የመጀመሪያወቹ ሰዎች ሆኑ። ኮሊንስ ባንጻሩ በጨረቃ ከባቢ በመብረር ከላይ ይጠብቃቸው ስለነበር ጨረቃን አልረገጠም። ይህ ድርጊት በፕሬዘደንት ኬኔዲ "የሰወች ልጅን ጨረቃ ላይ አሳርፎ በሰላም መመለስ" አላማ ያሳካ ነበር።

እቅድ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የመንኮራኩሩ ወደ ጠፈር መመንጠቅና ከንደገና መሬት ላይ ማረፍ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የአፖሎ 11 ሚሲዮን ወደ ጠፈር ሲመነጠቅ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰወች በአለም ዙሪያ በቴለቪዥናቸው ተመልክተውታል። ይህን ሚሲዮን ይዞ የተጓዘው ሮኬት ሳተርን ፬ ሲባል ችቦው እየተንቀለቀለ ወደ ሰማይ ጉዞ የጀመረው ኬኔዲ ጠፈር ማዕከል፣ 1961 ዓ.ም. ነበር። .

ሳተርን ፬ ሮኬት ጠፈርተኞቹን ይዞ ሲሄድ

መሬትን ከለቀቀ ከ2 ሰዓት በኋላ የጨረቃ ትዕዛዝ ማዕከልና ማረፊያ ሞጅሎቹ ዋናውን ሮኬት ለቀው በጠፈር ጉዞ ቀጠሉ። ከ3 ቀን በኋላ ትዕዛዝ ማዕከሉና ማረፊያው ሞዱል የጨረቃን ምህዋር ተከትለው ጨረቃን መዞር ጀመሩ። ከአንድ ቀን በኋላ ማረፊያው ሞዱል ከትዕዛዝ ማዕከሉ ተላቆ ጨረቃ ላይ አረፈ። በዚህ የማረፍ ተግባር ወቅት የኮምፒውተር ስህተት ስለገጠመ ማረፊያው ሞዱል በኔል አርምስትሮንግ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ስር ነበር። የሆኖ ሆኖ ለ25 ሰኮንዶች በቂ የሆነ ነዳጅ ሲቀር ማረፊያው መንኮራኩር ኔል አርምስትሮንግንና አልድሪንን ይዞ ጨረቃ ላይ በሰላም አረፈ።[1]

ጨረቃ ምድር ላይ የተከናወኑ ስራወች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

መንኮራኩሩ ጨረቃ ላይ እንዳረፈ የበዝ አልድሪን መጀመሪያ ተግባር ጸሎት ማቅረብ ነበር። አርምስትሮንግ ቀድሞ በመውጣ በጨረቃ ምድር ላይ የመጀመሪያው ሰው ሆነ። በዚህ ወቅት ከአፉ ነጥቆ የወጣው የመጀመሪያው ንግግር "ይህ ለአንድ ሰው ትንሽ ርምጃ ሲሆን ለሰው ልጅ ግን ታላቅ መመንጠቅ ነው" የሚል ነበር [2]

የኔል አርምስትሮን የመጀመሪያ ቃላት በጨረቃ ላይ (እንግሊዝኛ)

ለሚቀጥሉት ሁለት ሰዓታት አልድሪንና አርምስትሮንግ ፎቶ በማንሳት፣ ጽሁፍ በመጻፍና ናሙና እየቆፈሩ በመሰብሰብ ጊዜያቸውን አሳለፉ። ይህ ጉዳይ በወቅቱ በአለም ዙሪያ ለ6ሚሊዮን ሰወች ከአውስትራሊያ ራዲዮ ጣቢይ የተላለፈ ነበር [3]

የኔይል አርምስትሮንግ የእግር ኮቴ በጨረቃ

ጨረቃን መልቀቃቸውና ወደ መሬት መመለሳቸው[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ጨረቃ ላይ ስራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ሁለቱ ጠፈርተኞች ወደ ማረፊያ መንኮራኩራቸው በመመለስ ለ7 ሰዓት ጨረቃ ላይ ከተኙ በኋላ ከላይ በኮሊንስ ወደ ሚበረው የትዕዛዝ ማዕከል ለመብረር ዝግጅት ጀመሩ። በመሃሉ አልድሪን የሞተር ማቀጣጠያ ኤሌክትሪክ ሽቦን ሳያስበው ስለቆረጠ በጨረቃ ላይ ሊቀሩ ሆነ። ኔል አርምስትሮንግ ግን እስክርቢቶውን በመጠቀም ሽቦውን በማያያዝ ጠገነ። በዚህ ሁኔታ ከጨረቃ በመፈንጠር ከላይ ከኮሊንስ ጋር በትዕዛዝ ማዕከሉ ተገናኙ።

እነ አርምስትሮንግ በጨረቃ ላይ በነበሩበት ጊዜ ብዙ ቁሶችን ትተው ተመልሰዋል። ለምሳሌ ከ73 የአለም መሪወች የተላለፉ መልዕክቶችን፣ የሰላምታ መልክዕት በሁሉ የመሬት ላይ ቋንቋወችና የሁለት ሰው ልጆች ስዕሎችን ትተው ተመልሰዋል። የአሜሪካንንም ባንዲራ በጨረቃ ተክለዋል።

ሓምሌ 24 የትዕዛዝ ማዕከሉ መሬት ላይ ሲደርስ ምናልባትም ጠፈርተኞቹ ያልታወቀ አደገኛ ቫይረስ ጨረቃ ላይ አጋጥሟቸው ሊሆን ይችላል በሚል በኳረንታይን ለ3 ሳምንት ከሰው ልጆች ተለይተው ተቀመጡ። ከኳረንታይን ሲወጡ፣ በርግጥም እንደ ታላላቅ ጀግኖች በተለያዩ የአለም ክፍሎች ስማቸው ተጠራ በዋሽንግተን ዲሲና በሜክሲኮ ሲቲ ለጠፈርተኞቹ ትልቅ ሰልፍ ሆነ።

የተለያዩ ፎቶወች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ "Archive copy". Archived from the original on 2016-12-27. በ2010-12-07 የተወሰደ.
  2. ^ "Archive copy". Archived from the original on 2016-12-27. በ2010-12-07 የተወሰደ.
  3. ^ http://www.parkes.atnf.csiro.au/news_events/apollo11/pasa/on_eagles_wings.pdf