ኡድሙርትኛ

ከውክፔዲያ

ኡድሙርትኛ (удмурт кыл) የኡድሙርቶች ቋንቋ ነው። ኡድሙርቶች የኡድሙርቲያ ኗሪዎች ሲሆኑ ቋንቋቸው በፊኖ-ኡግሪክ ቋንቋ ቤተሰብ ውስጥ የተከተተ ነው። ኡድሙርቲያ በሩሲያ ውስጥ የሚገኝ ክፍላገር ሆኖ ኡድሙትኛ ከመስኮብኛ ጋራ መደበኛ ቋንቋዎቹ ናቸው። የሚጻፍበት በቂርሎስ ፊደል ነው። ቅርብ ዘመዶቹ ኮሚ እና ኮሚ-ፐርምያክ ቋንቋዎች ናቸው።

Wikipedia
Wikipedia