ኢሉማ-ኢሊ
Appearance
(ከኢሉማ-ኢል የተዛወረ)
ኢሉማ-ኢሊ (ወይም ኢሉማ-ኢሉም፣ ኢሉማን) በሱመር የባሕር ምድር ሥርወ መንግሥት (1645-1463 ዓክልበ.) መሥራች ነበር።
በ1645 ዓክልበ. አካባቢ የኢሲን ከንቲባ ኢሉማ-ኢሊ በሃሙራቢ ልጅ በባቢሎን ንጉሥ ሳምሱ-ኢሉና ላይ በዓመጽ ተነሣና ሥርወ መንግሥቱን መሠረተ። ነገሥታት ሱመርኛ ስሞች ቢወስዱም፣ ያንጊዜ መደበኛ ቋንቋ አካድኛ እንደ ሆነ ይመስላል።
ኢሉማ-ኢሊ ሳምሱ-ኢሉናን እንሳሸነፈው ይተረካል፣ ዓመት ስሞቹም በኒፑር ተገኝተው ኒፑርን ለጊዜ እንደ ያዘ ይታስባል። የሳምሱ-ኢሉና ተከታይ አቢ-ኤሹሕ ደግሞ ኢሉማ-ኢሊን ለማሸነፍ ሲሞክር ጠግሮስ ወንዝን ገደበ፤ ይህ ግን ስኬታም አሆነለትም። ኢሉማ-ኢሉ ከኤላም ጋራ ስምምነት አድርጎ ነጻነቱን ጠበቀ።
በአንድ ዝርዝር ጽላት ላይ ለ60 ዓመት እንደ ገዛ ሲል፣ የባሕር ምድር ሥርወ መንግሥት ድምር ከ182 ዓመታት ያሕል ወዳ 368 ዓመታት ስለ ደረበ፣ ምናልባት 30 ዓመት ብቻ ወይም 1645-1615 ያህል ገዛ።