ኢቱ
የኢቱ ( #Ituu/ Ittu) ህዝብ የኦሮሞ ብሄረ አካል የሆነ ህዝብ ነው። በበሬንቶ ቅርንጫፍ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን, ከአምስቱ የበሬንቱማ ኦሮሞ ልጅ አንዱ ከሆነው የመረዋ ልጅ ነው ። መረዋ የኢቱ አባት ሲሆን ኢቱ ወራያን (Warre) ጨምሮ አስር ጎሳን ያቀፈ ነው። የኢቱ ኦሮሞ ጎሳ መሬት ጨርጨር በመባል ይታወቃል። ጨርጨር ኦነ ኢቱ በማለት የሰፈሩበትን መሬት ይጠሩታል። ኦነ ኢቱ መለት የኢቱ ኦሮሞዎች ፖለቲካዊ ፣ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ና መንፈሳዊ ግዛት ማለት ነው። ኢቱ ኦሮሞ በዋናነት ሰፍረው የሚገኙት በምዕራብ ሀረርጌ ሲሆን ከፈንታሌ እስከ ወሎ ራያ ድረስ በስፈት ሰፍረው የሚገኙ የመረዋ ኦሮሞ ልጆች ናቸው ። የኢቱ ኦሮሞ ዋና መተዳደሪያ ማዕከል ጨፌ ኦዳ ቡልቱም ሲሆን ከአምስቱ ጥንታዊ የኦሮሞ ጨፌዎች መካከል አንዱ ሆኖ ይገኛል። ይህም ጨፌ ገዳ ኢቱ በመባል መቀመጫውን ኦዳ ቡልቱም በማድረግ ይታወቃል። ጨፌ ገዳ ኢቱ ማዕከል ጥንታዊ የምስራቅና ሰሜን ምስራቅ ኦሮሚያ ህዝብ, ማለትም የኢቱ ኦሮሞ፣ የአፍረን ቀሎ ፣ የሁምበና ና ራያ ኦሮሞዎች የፖለቲካ ና ማህበራዊ ማዕከል በመሆን በ15ኛው ና በ16ኛው ክፍለ ዘመን በኦሮሞ ህዝብ ታሪክ ውስጥ አኩሪ ሚና በማበርከቱ ግልቶ ሊታይ ችሏል። ወደ ምስራቁንና ሰሜን ኢ/ያ የተደረገውን የኦሮሞ ህዝብ መስፋፋት ዘመቻን ና ሂደቱን በከፍተኛ ብቃት የመሩት የኢቱ ኦሮሞዎች ና ጨፌያቸው እንደ ነበሩ አያሌ የታሪክ መዛግብቶች ያመለክታሉ ።
የኦሮሞ ህዝብ የገዳ ስርዓት ህጓችም የተሟሉበት በጨፌ ገዳ ኢቱ (ኦዳ ቡልቱም) እንደ ነበር የኦሮሞ አባ ገዳዎች ይናገራሉ። በኦሮሞ ገዳ ስርዓት ና በኦሮሞ ህዝብ ከቦታ ወደ ቦታ መስፋፋት ሂደት ውስጥ ቀድመው ወደ ምስራቅ የተንቀሳቀሱ መሆናቸው እንደ ፈር ቀዳጅ ይቆጠሩ ነበር። በገዲ ስርዓት ውስጥም የኢቱ ኦሮሞዎች እጅግ በጣም ጦረኛ ፣ ተዋጊ ና ጥሩ አመራር ሰጪ በመሆናቸው ይታወቃሉ። ይህም ከምስራቅ ሀረርጌ በሮዳ ከተማ አከባቢ አንስቶ እስከ አርሲ ኦሮሞ ድንበር የሚደርሰውን ሰፊውን ና ለምለሟ ከሀረርጌዋ ጨርጨር አንስቶ እስከ ራያዋ ጨርጨር ድረስ ሰፍረው እንዲገኙ ከማስቻላቸውም በላይ, የኦሮሞ ህዝብ ከባሌ ጀምሮ ወደ ምስራቅ ሲያደርግ የነበረውን የመስፋፋት እንቅስቃሴ ና ዘመቻን በብቃት በመምራት ኦሮሞ እስከ ሰሜን ሶማሊያ ድረስ እንዲዘልቅ አስችለዋል። ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የተደረገውን የኦሮሞ ህዝብ እንቅስቃሴ ከአዋሽ ማዶዋ የሀረርጌዋ ጨርጨር በመነሳት የሚሌ ፣ የባሺሎ ፣ የቡርቃ ወንዞችን በማቋረጥ በብቃት ና በተሳካ ሁኔታ ሰፊውን የወሎ ራያን የግጦሽ መሬት በመቆጣጠር እንደሰፈሩም የታሪክ ሙሁራኖች ይመሰክራሉ።
የወሎ ፣ ራያ ና የጨርጨር ኦሮሞ ህዝብ በኦሮምኛ ቋንቋ የአነጋገር ዘይቤም ፣ በባህላዊ አለባበስ፣ በመልልክ ፣ በኑሮ ዘይቤ፣ በአከባቢ ስም ስያሜዎች ና ያቀፋት የተለያዩ የጎሳ ቅርንጫፍ ስሞች ሳይቀር ከዬትኛውም የኦሮሞ ማህበረሰብ በላይ እጅግ በበለጠ ሁኔታ የተቀራረቡ የመሆናቸው ምስጥርም ከአንድ የኦሮሞ የቅርብ የዘር ሀረግ የመነጩ መሆናቸውን ብቻ ሳይሆን በእንድ ወቅት በአንድ በተመሳሳይ አከባቢ ይኖሩ የነበሩ ህዝቦች መሆናቸውን የሚያረጋግጡ ግብዓቶች ሊሆኑ ይችላሉ። ኢቱ የመረዋ ልጅ ናው።
ኢቱ የኢትዮጵያ ብሔር ነው።