ኢካሮስ

ከውክፔዲያ
የኢካሮስ ውድቀት፣ በ፲፭፻፶ በፒተር ብሮየል እንደተሳለ

ኢካሮስ እንደ ጥንቱ ግሪክ አፈ ታሪክ የታላቁ እጅ ጥበበኛ የ ዴድለስ ልጅ ነበር። ስለ ኢካሮስ ከተነገሩ ዋና ታሪኮች አንዱ ይኖሩበት የነበረውን ደሴት በረው እንዲያመልጡ፣ ዴደለስ ለልጁና ለራሱ ከሰምና ከወፎች ላባ አራት ክንፎች እንደሰራና ክንፎቻቸውን እየለበሱ እያለ ዳዲለስ ልጁን ኢካሮስን እንዲህ ብሎ እንዳስጠነቀቀው ነበር፦ «ወደ ፀሐይዋም ሆነ ወደ ባሕሩ እንዳትጠጋ፣ ይልቁኑ የኔን የበረራ መስመር ተከተል።»

አባትና ልጅ ክንፋቸውን እያራገቡ መብረር ሲጀምሩ ኢካሮስ ልቡ እንደሸፈተና በኋላም መሬትን እየለቀቁ ወደ አየሩ ሲቀዝፉ ኢካሮስ በደስታ እራሱን መቆጣጠር እንዳቃትው ታሪኩ ያትታል። የአባቱን ምክር ረስቶ፣ ወደ ሰማይ፣ ወደ ላይ ፀሐይን ተጠግቶ በመብረሩም ክንፉን አጣብቆ የያዝው ሰም በመቅለጡ ኢካሮስ ወደ ባሕሩ ወደቆ እንደተከሰከሰ አፈታሪኩ ያትታል። ይህ ባሕር እስከ አሁን ዘመን የኢካሮስ ባሕር ወይንም ኢካርያ ይባላል።[1][2][3]

አንድ አንድ ታሪክ አጥኘወች የዚህን አፈታሪክ መልዕት ሰዎች ከመጠን ያለፈ የገንዘብ፣ የስልጣልን፣ የመታዎቅ ወዘተ...ፍላጎት ባደረባቸው ጊዜ ውድቀታቸውም በዚያው ልክ ይፋጠናል እሚል ነው።

ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ Graves, Robert (1955). "92 – Daedalus and Talus". The Greek Myths. ISBN 0-14-007602-6. 
  2. ^ Thomas Bullfinch - The Age of Fable Stories of Gods and Heroes KundaliniAwakeningSystem.com Archived ጃንዩዌሪ 24, 2013 at the Wayback Machine & The Internet Classics Archive by Daniel C. Stevenson : Ovid - Metamorphoses - Book VIII + Translated by Rolfe Humphries - KET Distance Learning Archived ጁን 14, 2012 at the Wayback Machine 2012-01-24
  3. ^ Translated by A. S. Kline - University of Virginia Library.edu Retrieved 2005-07-03