Jump to content

ኢዛቤላ አቦት

ከውክፔዲያ
ኢዛቤላ አቦት
ኢዛቤላ አዮና አቦት

ኢዛቤላ አዮና አቦት (እ.ኤ.አ. ሰኔ 20፣ 1919 – ጥቅምት 28፣ 2010) የሃዋዪ ተወላጅ አስተማሪ፣ የስነ-ልቦና ባለሙያ እና ኤትኖቦታኒስት ነበረች። የመጀመሪያዋ በሳይንስ ፒኤችዲ የተቀበለች ሴት የሃዋዪ ተወላጅ ስትሆን [1]በፓሲፊክ የባህር ዋቅላሚዎች ላይ መሪ ባለሙያ ሆነች።[2]

የቀድሞሕይወት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አቦት ኢዛቤላ ካዋኬያ ያው ዩንግ አዮና (Isabella Kauakea Yau Yung Aiona) በሚል ስም ሰኔ 20 ቀን 1919 በሃና፣ ማዊ (ሃዋይ) ተወለደች። የሃዋይ ስሟ ትርጉም "የሃና ነጭ ዝናብ" ማለት ሲሆን "ሊዚ"[3] በሚል ቅጽል ስምም ትታወቅ ነበር። አባቷ የቻይና ዝርያ ያላቸው ሲሆኑ እናቷ ደግሞ የሃዋይ ተወላጅ ነበሩ። እናቷ ስለሚበሉ የሃዋይ የባህር አረሞች እና ስለ ሃዋይ አገር በቀል ዕፅዋት ጠቀሜታና ልዩነት አስተምረዋታል።[3] አቦት በስምንት ልጆች ቤተሰብ ውስጥ ብቸኛ ሴት ልጅ እና ሁለተኛዋ ታናሽ ነበረች።[4]


ትምህርት እና ትዳር

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ያደገችው በሆንሉሉ ዋይኪኪ አካባቢ ሲሆን፣ በ1937 ከካሜሃሜሃ ትምህርት ቤት ተመርቃለች። [1][3]በ1941[3] በሃዋይ ማኖአ ዩኒቨርሲቲ በቦታኒ (የዕፅዋት ጥናት) የመጀመሪያ ዲግሪዋን፣ በ1942 ከሚቺጋን ዩኒቨርሲቲ የማስተርስ ዲግሪዋን፣ እንዲሁም በ1950[2] [3]ከካሊፎርኒያ በርክሌይ ዩኒቨርሲቲ በዚሁ የትምህርት መስክ የዶክትሬት ዲግሪዋን (PhD) አግኝታለች።

በሃዋይ እና በበርክሌይ ዩኒቨርሲቲ አብሯት ተማሪ ከነበረው የሥነ-ሕይወት (zoologist) ባለሙያ ዶናልድ ፑትናም አቦት (1920-1986) ጋር ትዳር መሰረተች። ባልና ሚስቱ ወደ ፓስፊክ ግሮቭ፣ ካሊፎርኒያ የተዛወሩ ሲሆን ባሏ በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ[5] በሚተዳደረው የሆፕኪንስ ማሪን ስቴሽን ያስተምር ነበር።


ሙያዊ ተግዳሮቶች እና ፈጠራዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በዚያን ጊዜ ሴቶች ለአካዳሚክ የሥራ መደቦች ብዙም የማይታጩ በመሆናቸው፣ ልጇን አኒ አቦት ፎርስተርን በማሳደግ እና የካሊፎርኒያን የባህር ዳርቻ አረሞች (algae) በማጥናት ጊዜዋን አሳልፋለች። የአካባቢውን የባህር አረም (bull kelp) ለምግብነት እንዲውል በማድረግ እንደ ኬክ እና ኮምጣጤ (pickles) [3]ባሉ ምግቦች ውስጥ ለመጠቀም የምግብ አዘገጃጀት ዘዴዎችን ቀይራለች።

  1. 1 2 Michael Tsai (July 2, 2006). "Isabella Abbott". Honolulu Advertiser. Retrieved November 4, 2010
  2. 1 2 Kevin Howe (November 17, 2010). "'Seaweed lady' Isabella Abbott dies: Scientist studied algae at Hopkins Marine Station". Monterey Herald. Archived from the original on February 1, 2014. Retrieved December 8, 2010
  3. 1 2 3 4 5 6 Bergeron, Louis (December 7, 2010). "Isabella Abbott, world-renowned Stanford algae expert, dies at 91". Stanford Report. Stanford University. Archived from the original on June 2, 2013. Retrieved December 7, 2010.
  4. Crites, Jennifer (October 21, 2010). "Pioneering professor is first lady of limu". Malamalama: The Light of Knowledge. University of Hawaiʻi. Archived from the original on March 30, 2023. Retrieved November 4, 2010.
  5. Blinks, Lawrence; Giese, Arthur C.; Pittendrigh, Colin (1986). "Memorial Resolution: Donald Putnam Abbott 1920–1986" (PDF). Hopkins Marine Station. Stanford University. Archived from the original (PDF) on July 5, 2010. Retrieved December 8, 2010.