እየሩሳሌም
(ከኢየሩሳሌም የተዛወረ)
Jump to navigation
Jump to search
ኢየሩሳሌም (ዕብራይስጥ፡- ירושלים ፤ አረብኛ፦ القـُدْس) የእስራኤል ዋና ከተማ ናት። በእስራእል ትልቁ ከተማ ስትሆን የምትገኝው በስተምሥራቅ በኩል ነው። በ3 ሃይማኖቶች (ለአይሁድና፤ ለክርስትና እና ለእስልምና) በጣም የተቀደሰች ናት። የድሮ ታሪኮች ስለሞሏት፣ ብዙ ሰዎች ቱሪስት ሆነው መጥትው ያዩዋታል።
እስራኤል በ1949 እ.ኤ.አ. ዋና ከተማነቱን ከቴል አቪቭ ወደ ምዕራብ ኢየሩሳሌም አዛወረች። በ1967 እ.ኤ.አ. በተዋጀ ጦርነት ምሥራቅ ኢየሩሳሌምን ደግሞ ያዘች። በ1980 እ.ኤ.አ. እስራኤል ሙሉ ከተማውን ዋና ከተማዋ ሆኖ ሾመችው። ነገር ግን አብዛኛው አገራት ይህን አድራጎት ሳይቀበሉ ኤምባሲዎቻቸው እስካሁን በቴል አቪቭ ናቸው የሚገኙ። ፍልስጤም ደግሞ ዋና ከተማውን አድርጎታልና ዛሬም በጣም ተቃራኒ ጉዳይ ሆኗል።
በ2017 እ.ኤ.አ. (2009-2010 ዓም) ሩስያ፣ አሜሪካና ጓቴማላ ለምዕራብ ኢየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ እንዲሆን ዕውቅና ሰጡ። አንዳንድ አገራት ደግሞ ለምሥራቅ ኢየሩሳሌም የፍልስጤም ግዛት ዋና ከተማ እንዲሆን ዕውቅና ሰጡ።
የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 695,500 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 31°47′ ሰሜን ኬክሮስ እና 35°13′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |