ኤማጥዮስ
Appearance
ኤማጥዮስ፣ ኤማጦስ ወይም አማጦስ (ግሪክ፦ Ήμαθος፣ `Αμαθος) በአፈ ታሪክ ዘንድ የኤማጥያ መስራችና መጀመርያ ሰፈረኛ ነበረ። ኤማጥያ በኋላ መቄዶን የተባለው አገር ጥንታዊ ስም ነበር።
ማርስያስ ዘፔላ (340 ዓክልበ. ግድም የጻፈ) እንዳለው፣ አማጦስና ፒዬሮስ የማከድኖስ ልጆች ሆነው ኤማጥያና ፒዬሪያ የተባሉት ሠፈሮች ስለነርሱ ተሰየሙ።
ሶሊኑስ (210 ዓ.ም. ግድም) እንደሚለን ግን፣ ኤማጦስ የማከድኖስ ዘመድ ሳይሆን ከማከድኖስ ዘመን በፊት ይኖር ነበር። አገሩ ገና ኤማጥያ እየተባለ ኦሬስቴስና ሄርሚዮኔ በዚያ ደርሰው ልጃቸውን ኦረስቲስን ወለዱ፣ እርሱም እስከ አድሪያቲክ ባሕር ድረስ የዘረጋ በስሙ ኦረስቲስ የተባለ ግዛት አቆመ። በሶሊኑስ ዘንድ ይህም ሁሉ ከማከድኖስ አስቀድሞ ሆኖ ነበር።
ስቴፋኖስ እንደሚጽፍ፣ ብሩሲስና ጋላድራይ የተባሉት ሠፈሮች በዚሁ ኤማጦስ ልጆች ብሩሶስና ጋላድሮስ ተመሠረቱ።
አንዳንድ ክርስቲያን ሊቃውንት የዚሁ አምጦስ መታወቂያ እና በኦሪት ዘፍጥረት 10 የተጠቀሰው አማቲ (የከነዓን ልጅ) አንድላይ ነው ብለዋል።
በግሪክና በሮማይስጥ ቅኔ የመቄዶን ሌላ ስም «ኤማጥያ» በመሆኑ፤ «ኤማጥዩስ» ደግሞ የታላቁ እስክንድር ቁልመጫ ስም ሊሆን ይችላል።