ኤድመንድ ሁሠርል
Appearance
(ከኤድመንድ ኸስረል የተዛወረ)
ኤድመንድ ጉስታቭ አልብሬክት ሁሠርል (ሚያዚያ 8, 1859 እ.ኤ.አ. – April 26, 1938 እ.ኤ.አ.) ኦስትሪያ ተወልዶ ጀርመን ያረፈ ፈላስፋና የሥነ ክስተት (ፌኖሜኖሎጂ) መስራች ነበር። በጊዜው ይሰራበት የነበረውን የፖዚቲቪስት አስተሳሰብ በመካድ ተመክሮ የሁሉ ዕውቀት ምንጭ ነው በማለት የራሱን ፍልስፍና ያራመደ ሰው ነበር።
ሁሠርል ከካርል ዌይስትራስ ሂሳብ በመማር ዶክትሬት ያገኘ ሲሆን ፍልስፍናም እንዲሁ አጥንቷል። ከዚያም የፍልስፍና አስተማሪ ሆኖ ሰርቷል።
ሁሠርል በምናባዊ ክስተትና በተጨባጭ አለም ክስተት መካከል ያለው ልዩነት ትኩረት (ኢንቴንሺናሊቲ) እንደሆነ አስረድቷል። በሁሠርል አስተያየት ማናቸውም የአዕምሮ ስራወች ትኩረት አላቸው ማለትም ማናቸውም እምነቶች ወይም ፍላጎቶች ወይንም ሃሳቦች ስለ አንድ ነገር ወይም ስሌላ ነገር ነው። ያ ነገር ትኩረታቸው ነው። ነገር ግን ተጨባጩ አለም እንዲህ ያለ ትኩረት የለውም።
በሌላ በኩል ሁሠርል በደንበኛና ደንበኛ ያልሆነ አቀራረብ ባላቸው የነገር አቀርቦት ላይ ጽፏል። ለምሳሌ አንድ ቤት ፊት ለፊት የቆመ ሰው ቤቱን በደንበኛ አቀራረብ ይገነዘባል። በተጻራሪ ከሌላ ቦታ ሆኖ አድራሻ ሲጠይቅ እዚህ እዚህ ቦታ ላይ ይገኛል ሲሉት «ደንበኛ ያልሆነ» አቀራረብ በማለት ይተነትናል።