እምቧጮ

ከውክፔዲያ
እምቧጮ

እምቧጮ (Rumex nervosus) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

እስከ 2 ሜትር የሚደርስ ቊጥቋጥ፣ ብዙ አገዶች ከመሬት ይነሣሉ፣ ልጡ ቡላማ፣ ቅጠሎች ትንሽ ውሃማ ናቸው።

አስተዳደግ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ድካም ደረቅ አፈር ይመርጣል።

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በማናቸውም ከፍታ ይገኛል፣ በመንገድ ዳር፣ በተፈጀ መስክ። በድሬ ዳዋ አካባቢ ያለው ደንገጎ ተራራ ከዚህ ተክል ኦሮምኛ ስም (ደንገጎ) ነው።

የተክሉ ጥቅም[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ቅጠሉ አገዳውም በሰፊ ጫትን ለመጠቅለል ይጠቀማል። ወፍራም፣ ውሃማው ቅጠሎች ጫትን ለረጅም ጊዜ ይጠብቃሉ።

ውሃማው ቡቃያ በእረኞች ይበላል። ቡቃያው ቶሎ፣ ለኣጭር ጊዜ፣ በእሳት ውስጥ ቢሳክ፣ ለስላሳ ይሆናልና በልጆች ይወደዳል።

የአገዳው ከሰል ከእንቁላል አስቋል ተቀላቅሎ የቆዳ መቃጠል ለማከም ይጠቀማል። ቅቤም ይጨመራል። [1]

የእምቧጮ ቅጠልና አገዳ በሎሚ ጭማቂና ውሃ ተደቅቆ ለብጉርና ለእከክ ይቀባል።[2]

የእንቧጮ ሥር ዱቄት በኪንታሮት በተቈረጠው ጫፍ ላይ ለማከም ይደረጋል። የሥሩም ዱቄት ከተቀለጠ ቅቤ ጋር ለተቅማጥ ይጠጣል። ሥሩም በማር ለጥፍ ለሆድ ቁርጠት ይበላል።[3]


  1. ^ አማራ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE Archived ጁላይ 31, 2017 at the Wayback Machine March 1976 እ.ኤ.አ.
  2. ^ የፍቼ፣ ኦሮሚያ ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 2006 ዓም ከዓቢዩ እኒየው እና ሌሎች፣ ጎንደርና አዲስ አበባ ኡኒቨርሲቲዎች ሥነ ፍጥረት ኮሌጆች
  3. ^ በደብረ ሊባኖስ ዙሪያ ያለው ሕዝብ መድሃኒታዊ እጾች እውቀናና ጥቅም 1998 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ ግርማይ መድኅን፣ ያለም መኮነን፣ አዲስ አበባ ዩኒቬርሲቴ፣ አክሊሉ ለማ ተቋም