Jump to content

እርግጥ

ከውክፔዲያ
(ከእርጉጥ የተዛወረ)

እርግጥሒሳብ ወይም በሥነ-አምክንዮ ሲተረጎም የአምክንዮን ህጎች ተጠቅመን ያረጋገጥነው አረፍተ ነገር ማለት ነው። የምናረጋግጠው እንግዲህ እሙኖችወይም ሌሎች እርግጦችን በአምክንዮ እያጣመርን በማያያዝ ነው። የሂሳብና አምክንዮ አረፍተ ነገሮች ብዙውን ጊዜ የሚረጋገጡት የጥገኛ አምክንዮ ዘዴን በመጠቀም ነው። ለዚህ ምክንያቱ የእርግጡ አረፍተ ነገሮች ከአንድ መነሻ አርፍተነገርና ከዚያ አረፍተ ነገር ላይ ጥገኛ ከሆነ አርፍተ ነገር ስለሚሰሩ።

ለምሳሌ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

እሙን ፩ ፡ በሁለት ነጥቦች መካከል ከሚሳሉ ማናቸውም መስመሮች፣ ቀጥተኛ መስመር በጣም አጭር ነው። ይህ እንግዲህ ግልጽ የሆነ ዓረፍተ ነገር ስለሆነ እሙን ይባላል። የሚከተለውን እርግጥ እንመልከት፦

እርግጥ 1 ፡ የሶስት ማዕዘን ሁለት ጎኖች ሲደመሩ ምንጊዜም ከሦስተኛው ጎን ይበልጣሉ።

ማረጋገጫ

የሶስት ማዕዘኑን መጋጠሚያ ነጥቦች ሐ፣ ለ፣ መ እንበላቸው።
ከሐ እስከ መ የተዘረጋው ቀጥተኛ መስመር ከሐ እስከ መ ከሚዘረጉ ማናቸውም ሌሎች መስመሮች ያንሳል ..... በእሙን ፩
ስለዚህ መስመር ሐመ ፣ ከ ሐለ+ ለመ መስመሮች ድምር ያንሳል .... ከላይ በተሰጠው ማረጋገጫ
ይህ ሃሳብ ለማንኛውም ነጥብ ስለሚሰራ፣ ርጉጥ፩ ትክክል ነው ማለት ነው። ..... ማረጋገጡ ተፈጸመ።