እሳት የማያጠፋው ውሀ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

እሳት የማያጠፋው ውሀ፡ . . ሰውየው ዳብዳቤ በመጻፍ ላይ ሳለ፡ ሠራተኛው በሩን በርግዳ ትገባና "ጌታዬ፡ ማድቤቱ በእሳት ተያይዟል" ትለዋለች። ባለቤትየው ገስግሶ እማድቤቱ ሲደርስም መለስተኛ እሳትና ምድጃው ላይ ተጥዶ የሚንከተከተውን ድስት ሙሉ ውሃ ያያል። በዚህ ጊዜ ተናዶ "አንች ደደብ፡ ወደኔ ከመምጣት ይልቅ የሚፍለቀለቀውን ውሃ አታፈሽበትም ኖሯል?" በማለት ቢገስጻት "ጌታዬ ውሃው'ኮ የፈላ ስለሆነ አያጠፋውም ብዬ ነው" ብላ አሳቀችው።