እሸ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
የእሸ ዛፍ
የእሸ ፍሬ ከጎንጅ ቆላላ ወረዳ

እሸ Mimusops kummelቆላማና ወንዝ ዳር እሚበቅል ተክል ነው ።እሸ ፍሬያቸው ለምግብነት ከሚውሉ ሀገር በቀል ዕፅዋቶች ውስጥ አንዱ ነው።የእሸ ዛፍ በቁመቱ ከትልልቅ የዛፍ ወይም እፅዋት ዓይነቶች አንዱ ነው። ቅጠሉ መጠነኛና ጌሾ መሰል ነው።ፍሬው በለጋነቱ የመርዝ ዛፍ ፍሬ ይመስላል። ፍሬው ሲቀላ ለምግብነት ይውላል።በተለይ የእሸ ፍሬ ሲለሞጭ ወይም በሚገባ ሲቀላ እና የቀላውን ደግሞ በመቁላት፡ በጨው ውሃ አሽቶና ደብኖ ሲመገቡት እጅግ ይጣፍጣል[1]

ዛፉ ጥላ በመሆን ከስሩ ሌሎች ተክሎች እንዳይጠወልጉ ይረዳል። ግንዱ ደግሞ ጠንካራ ስለሆነ ለግንባታ፣ የቤት ቁሳቁስ ለማምረቻነትና እና ለንብ ቀፎ መስርያ ያገለግላል።

ተጨማሪ ንባብ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ የጎንጅ ቆላላ ወረዳ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል