Jump to content

እያሳራኝ ነው

ከውክፔዲያ

እያሳራኝ ነው

(8)አንድ ከዚህ በፊት የተረቡት ሰው መንገድ ላይ አግኝቷቸው ሊደብደብ ሲያባርራቸው እሳቸውም ሲሮጡ ቆይተው ሊደርስባቸው ሲሆን ቶሎ ብለው ሱሪያቸውን ፈተው ለመጸዳዳት ቁጭ ይላሉ። አለቃ በነበሩበት ዘመን ይትባሃሉ ሰው ጠላትም ቢሆን የሚገደለው፤ የሚደበደበው ከነሱሪው እንጂ ሱሪ አውልቆ አይደለም። ይሄ ወንድነትንም አያሰኝም። መለኛው አለቃ ይቺን ሰሩዋ። ሰውየውም ሊነርታቸው (ሊያሳራቸው) እስኪነሱ አጠገባቸው ቆሞ ይጠብቃል። እሳቸው ቁጭ እንዳሉ ሰውየው እንደቆመ ሁለቱን የሚያውቅ ሰው በመንገዱ ሲያልፍ ሰላም ብሏቸው የሁለቱ ነገር ገርሞት «ምን እያደረጋችሁ ነው?» ይላቸዋል። አለቃም ፈጠን ብለው «እያሳራኝ ነው።» ብለው መለሱ። ሊደበድባቸው የነበረው ሰውዬ በመልሳቸው ስቆ ትቷቸው ሄደ አሉ።