እዮብ መኮንን
እዮብ መኮንን፣ ኢትዮጵያዊ ታዋቂ ዘፋኝ የነበረ ሲሆን ብዙ ዘመናዊ የሙዚቃ ስራዎችን አቅርቧል። ከነዚህም ዉስጥ ለኢትዮጵያ የሬጌ ሙዚቃ እድገት አስተዋፆ ያደረገበት ስሙን በጉልህ ያስጠራዋል። እዮብ መኮንን ባደረበት ድንገተኛ ህመም፣ በናይሮቢ ከተማ ሕክምናውን በሚከታተልበት ሆስፒታል እሁድ ማታ ነሐሴ ፲፪ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. አርፏል።[1]
እዮብ መኮንን እባላለሁ በነገራችን ላይ የወታደር ልጅ ነኝ አባቴ ወታደር እንደመሆኑ ከሀገር ሀገር በመዘዋወር ነበር ሀገሩን ያገለግል የነበረው ይኸው ሥራው ደግሞ ጂግጂጋ አድርሶት ከእናቴ ከአማረች ተፈራ የምሩ ጋር ለመተዋወቅ በቃና ጥቅምት 2 ቀን 1967 ዓም በጭናቅሰን ገብርኤል ጂግጂጋ ከተማ እኔ ተወለድኩ ዕድሜዬ ለትምህርት እንደደረሰም የአንደኛ ደረጃ ትምህርቴን በጂግጂጋ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከፈል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ደግሞ ከአባቱ ከመኮንን ዘውዴ ይመኑ ጋር ወደ አስመራ በመሄድ የተከታተልኩ ሲሆን ቀሪውን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ደግሞ ወደ ጂግጂጋ በመመለስ ተከታትያለሁ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን እየተከታተልኩ የሙዚቃ ፍቅር የገባቸው እና ሙዚቃን ከኔ በተሻለ ከሚሠሩ ልጆች ጋር በአቅራቢያዬ እየሄድኩ እለማመድ ጀመር ነገር ግን ለሙዚቃው አዲስ እንደመሆኔ መጠን በሙዚቃ መሣሪያ ከሚለማመዱት ልጆች ጋር እኩል ሙዚቃን መለማመድ አዳጋች ሆኖብኝ ነበር ይህንንም ለአብሮ አደግ ጓደኛዬ ሙዚቃን እየተለማመድኩ እንደሆነ እና ነገር ግን ከመሳሪያው እኩል ስጫወት ልከ እንደማይመጣልኝ እና መሣሪያው የሚያወጣው ድምፅም እንደሚረብሸኝ ስነግራት እሷም ግዴለህም እዮብ መዝፈን እንደምትችል እኔ በደንብ አውቃለሁ አንድ ቦታ ልውሰድህ አለችኝ እኔም እሺ ስላት በማግስቱ ሙዚቃን በተሻለ መልኩ የሚለማመዱ ሊጆች ጋር ይዛኝ ሄዳ አስተዋወቀችኝ። በሰዓቱ ስለ ሪትም ፣ ፒች ወዘተ የማውቀው ነገር አልነበረም ይህን ሁሉ ሳላውቅ ልጆቹ በሚለማመዱበት ቦታ ላይ ተገኘሁና በል ዝፈን ተባልኩ እኔም የቦብ ማርሊን ኖ ውመን ኖ ከራይ የሚለውን ዘፈን ሳንቆረቁርላቸው በጣም ወደዱኝ እና በዚያው አብሬያቸው እንድለማመድ ፈቀዱልኝ የሚጨመረውን ጨምሬ የሚቀነሰውንም ቀንሼ ከቀናት ልምምድ በኋላ መድረክ ላይ ይዘውኝ ወጡ መድረክ ላይ በወጣሁ የመጀመሪያው ቀን ሕዝቡ ተሸከሞኝ አብሮኝ ሲደሰት ዋለ። ያኔ መዝፈን እንደምችል ገባኝ በዚህ ጊዜ ከሙዚቃው ጎን ለጎን ራሴንም ሆነ ቤተሰቦቼን የምረዳው ከቦታ ቦታ እየተዘዋወርኩኝ በማነሳቸው ፎቶግራፎች አማካኝነት ነበር ፎቶ ግራፎቼን ለማሳጠብ ሐረር በምሄድበት ጊዜ ናሽናል የተባለ ሆቲል እየተጋበዝኩ እዘፍን ነበር። በዘፈንኩ ቁጥር ደግሞ ሽልማቱ በሽ በሽ ነው:: በዚህ ወቅት አሸናፊ ከበደ እነ ታምራት ደስታን ይዞ ጂግጃጋ መጣ እኔም ገና እንዳየኋቸው ዝም ብሎ ደስ አለኝ። መዝፈን መቻሌን ማወቁ ለዘፋኞች ልዩ ፍቅር እንዲኖረኝ አድርጎኛል። አዲስ አበባ ገብቶ የመዝፈን ጉጉቴም ከፍተኛ ስለነበር መዝፈን እንደምችል ነገርኳቸው እና አዲስ አበባ ይዛችሁኝ ካልሄዳችሁ ብዬ ለመንኳቸው እነሱ ግን አንተ እዚህ ጥሩ ኑሮ ነው ያለህ እዚያ ሄደህ ምን ታደርጋለህ ብለው መከሩኝ። እኔም ግዴላችሁም አላሳፍራችሁም ውሰዱኝ ብዬ ደጋግሜ ለመንኳቸው ነገር ግን ሁኔታዬ ስላላማራቸው ሥራቸውን ሠርተው ከጨረሱ በኋላ ጥለውኝ ጉዟቸውን ቀጠሉ። በዛው ሰሞን (1991 ዓ.ም) ሐረር ያነሳኋቸውን ፎቶግራፎች እያሳጠብኩ አብሮኝ ፎቶ ግራፍ ያነሳ የነበረን አንድ ልጅ ድንገት አገኘሁት (ስሙን ባልጠቅሰው ይሻላል) ያ ልጅ ሥራው አልሆንልህ ብሎት ከስሮ በነበረ ጊዜ እኔ ፎቶ ካሜራ ሰጥቼው ነው እንደገና ሥራ ያስጀመርኩት። ከልጁ ጋ እንደተገናኘን ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ወሬ ስንጀምር መሻሻሉን እና ጉርሱም የምትባል ሀገር ፎቶ ቤት መከፈቱን ነግሮኝ እንደውም እዛ ከአዲስ አበባ የመጡ ዘፋኞች ሙዚቃ እያቀረቡ ስለሆነ ለምን አንሄድም አለኝ፡ በወቅቱ ኪሴ ውስጥ ሁለት ብር ብቻ ነው የነበረኝ እና ብር እንዳልያዝኩ ስነግረው አንተ ባለውለታዬ ነህ እኔ ሁሉንም ነገር እችልሀለሁ አለኝና ተያይዘን በሀይሉከስ ተጭነን ጉርሱም ገባን። እዚያ ስንደርስ አሁንም እነ አሸናፊ ከበደ ሙዚቃ እያቀረቡ ነው። በድጋሚ ሳገኛቸው ደስ ብሎኝ በድፍረት አስዘፍኑኝ አልኳቸው፡፡ እነሱም በመገረም አዩኝና እዚህም መጣህ አሉኝ እኔም አዎ አልኳቸው እና በድጋሚ እንዳ ዘፍኑኝ ለመንኳቸው እነሱም እሺ አሉና ዕድሉን ሰጥተውኝ መድረክ ላይ ወጥቼ ስዘፍን በሽልማት ተንበሸበሽኩ። እነ አሸናፊም ይህን ሲያዩ እሺ አዲስ አበባ ብንወስድህ ማን ጋር ታርፋለህ አሉኝ እኔም ካዛንቺስ አክስት ስላለችኝ እሷ ጋር ማረፍ እንደምችል ስነግራቸው ተስማሙና ይዘውኝ ጉዞአቸውን ቀጠሉ። እነሱ በየደረሱበት ሀገር አብሬ እየዘፈንኩ እና ፎቶ እያነሳሁ ከብዙ ቀናት ጉዞ በኋላ በ24 ዓመቴ አዲስ አበባ ገባሁ። አዲስ አበባ ካዛንቺስ አካባቢ አክስቴ ጋር ባረፍኩበት ወቅት የሀይልዬ ታደሰ ይሞታል ወይ የሚለው አልበሙ አዲስ ስለነበር በየጉራንጉሩ ሁሉ ይደመጥ ነበር። አዲስ አበባ በገባው በነጋታው አክስቴ ከኃይልዬ ጋር ትግባባ ስለነበር እሱ ናይት ክለብ እንድሠራ እንድታስፈቅድልኝ ስጠይቃት ያለምንም ማንገራገር ክለቡ ድረስ ሄዳ ስለእኔ ነገረችው። በነጋታው ኃይልዬ አስጠራኝና መዝፈን ትችላለህ አለኝ እኔም በደንብ እንደምችል እርግጠኛ ሆኜ ነገርኩት እሱም እንድሞከር እድሉን ሰጠኝ። ቀደም ሲል እንደገለፅከት ስለ ሪትም አጠባበቅና ስለሌላውም ነገር ምንም እውቀት ስለሌለኝ ገና ኪቦርድ ሲከፈት አብሬ መጮህ ስጀምር ይሄ ገና ይቀረዋል ብለው ገሸሽ አደረጉኝ እኔም የመገለል ስሜት ተሰምቶኝ ወጣሁና እዛ ቤት ዳግመኛ ሳልሄድ ቀረሁ። ለተወሰኑ ቀናት እቤት ቁጭ ብዬ እያንጎራጎርኩ ማንን ልጠይቅ ማንን ላናግር ማን ያዘፍነኝ በሚል ሀሳብ ተወጠርኩ ሌሎች የከለብ ባለቤቶችን ፈልጌ ማናገር እንዳለብኝ ራሴን አሳመንኩት ነገር ግን አንድ ምሽት ላይ የኔን ህይወት የሚቀይር ከስተት ተከሰተ በዛች የተባረከች ምሽት ፋልከን ክለብ ውስጥ ብዙ የውጭ ሀገር ዜጎች ሊዝናኑ ስለመጡ እንግሊዝኛ ዘፈን የግድ አስፈላጊ ስለነበር ተጠራሁ ጆሮዬን ባለማመን በፍጥነት ከተኛሁ ተነስቼ ወደ ክለቡ በመሄድ ጃምቦ ፋና የሚለወንና ሌሎች የአፍሪካ አ እንግሊዝኛ ዘፈኖችን እየሰባበርኩ አስነካሁት ከዛ ምሽት በኋላ ይሄ ለ ጎበዝ ነው ተባልኩና በወቅቱ የሀይልዬ ታደሰ ማናጀር በነበረው ወንድ አማካኝነት በደመወዝ ተቀጠርኩ፡ ከዛች ቀን በኋላ ኦሮሚኛውን ሱማሊኛውን፤ እንግሊዝኛወን የተጠየኩትን ቋንቋ ሁሉ እየሰባበርኩ መጫወት ጀመርኩ። ሰው እየወደደኝና አየተቀበለኝ ሄደ። እንደ አጋጣሚ የአከስቴም ቤት ፋልከ ከለብ አጠገበ ስለነበር ኑሮዬን አክስቴም ጋር ፋልከን ከለብ ውስጥም በማድረግ የአዲስ አበባን ኑሮ ተያያዝኩት። በ991 ዓ.ም ሙዚቃን እንደ ፕሮፌሽን ሀ ብዬ ፋልከን ከለብ ውስጥ በስፋት መጫወት ጀመርኩኝ በከለብ ህይወቴም በዋነኝነት የአሊ ቢራና የቦብ ማርሌን ዘፈኖች በስፋት አቀነቅን ነበር። ኦሮሚኛ መስማት እና መናገር ስለምችል ነው መሰለኝ ከሀገር ወስጥ ድምፃውያኖች ለአሊ ቢራ ልዩ ፍቅር አለኝ፡ የአሊ ቢራን ዘፈኖች ህፃን ሆኜ ወደ ትምህርት ቤት ስሄድ እያንጎራጎርኳቸው ስለምሄድ ልክ እንደ ህዝብ መዝሙር ሸምድጃቸው ነበር። ለብዙዎቹ የሀገራችን አርቲስቶች ፍቅር አ ክብር አለኝ ለባህል እና ሀገራዊ ሙዚቃዎች ግን ጌቴ አንለይን የመጀመሪያው ረድፍ ላይ ነው የማስቀምጠው ለሱ ልዩ ፍቅር አለኝ የቃላት አጠቃቀሙ ጉልበቱ የድምፁ ወብት ይማርከኛል። በተለይ ሀገሬን ስለምወድ ነው መሰለኝ ምናለኝ ሀገሬን በተለየ ሁኔታ እወዳታለሁ። ከዛ ውጪ ግን ብዙ ጊዜ መጽሀፍ ቅዱስ ማንበብ ያስደስተኛል። ልከ እንደ አሊ ቢራ ሁሉ ቦብም ሮል ሞዴሌ ነው። ቦብ ማርሌ ማለት ገላጭ ዘፋኝ ነው። ከቦብ በዜማ እንዴት ስሜት እንደሚገለፅ በደንብ ተምሬአለሁ። ቦብ ዜማን ከግጥሙ ጋር አብሮ ሲተርከው ከትርነቱ ቦታ ላይ ነው ቀጥታ በመንፈስ የሚወስደኝ። ቦብ ሲዘፍን ትንፋሽ አወሳሰዱ በስሜቱ ማዘኑን እና መቆጣቱን መግለፅ የሚችል ትልቅ ድምፃዊ ነው። እኔም እነዚህን ቴከኒኮች ከቦብ ማርሌይ የወረስኩት ይመስለኛል። ልክ እንደቦብ ማርሊ የሬጌን ዘፈኖች በደንብ ስለምጫወት እና ፀጉሬም ወደ ቦብ ይሄድ ስለነበር አድናቂዎቹ እና የሰፈር ልጆች ቦብ ብለው ነበር የሚጠሩኝ።
መረጃውን ያጋራዋችሁ የአብስራ አለሙ ነኝ
ለበለጠ መረጃ በቴሌግራም @eyobmekoneny ላይ ያግኙኝ
አምላክ ነብስህን በገነት ያኑርልን ኢዮባችን
>የፍቅር አኩኩሉ(ሲንግል)
የመጀመሪያ አልበሙ "እንደ ቃል"
>ትወደኛለች
>ይዘባርቃሉ
>ያየሽውን አይቻለሁ
>infaa gati nara(ኦሮምኛ)
>ግን በምን በለጥሻቸው
>ደስተኛ ነኝ ከ ዘሪቱ ከበደ
>ታሚኛለሽ አሉ
>ይገርማል
>ወኪል ነሽ
>ውል አይፃፍ
>ነቅቻለሁ
>ነገን ላየው
ሁለተኛው አልበሙ
የአልበሙ መጠሪያ "እሮጣለሁ" ሲሆን በውስጡ 14 ሙዚቃወችን የያዘ ነው
- ሰማኋቸው *ትክክል ነሽ *ተጠርቸ *የጋበዝኳቸው *wehajira(አፋርኛ) *ወደናቴ ቤት *ማን ያውቃል
- ተው ያልሽኝን ተውኩት *አንደበቴ *ሳይ *ይለፍ *ዝም እላለሁ *እንዴት ብየ
- እሮጣለሁ
- ^ ሪፖርተር ጋዜጣ Archived ኦገስት 22, 2013 at the Wayback Machine (በነሐሴ ፳፭ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. የተወሰደ)
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |