እግዚዕ

ከውክፔዲያ

እግዚዕግዕዝ ቋንቋ ጌታ ወይም አለቃ ማለት ነው። ይህ ቃል በመጽሐፍ ቅዱስግሪክኛ Κύριος የሚለውን የማዕረግ ስም ለመተርጎም አገልግሏል።

በግዕዝ "እግዚእት" ማለትም እመቤት ማለት ሲሆን "እግዚእትነ" ማለት "እመቤታችን" የሚለውን የማዕረግ አጠራር ለማመልከት ይሰራበታል።

በዚህም መሰረት "እግዚአብሔር" የሚለው የአማርኛ / የግዕዝ ቃል ከዚህ መሰረታዊ ቃል የተገኘ ሲሆን የፈጣሪን የተጸውዖ ስም (ማለትም ይሖዋ ወይም ያህዌ የሚለውን) በመተካት በአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ውስጥ ተሰርቶበታል።