እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር

ከውክፔዲያ
(ከእ.አ.አ. የተዛወረ)

እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር ወይም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር (በአጭሩ እ.አ.አ.) የሚለው ሃረግ ከፊቱ ወይም ከኋላው የተጠቀሰው ዓመት በተለምዶው የአውሮፓውያን የሚባለው እና በግሪጎሪ አስራ ሦስተኛ (እንግሊዝኛ: Pope Gregory XIII) የተጀመረውን የግሪጎሪያዊያን አቆጣጠር መሆኑን ይገልጻል።

በብዙ አገራት ይህ በሮማይስጥ ስሙ አኖ ዶሚኒ (Anno Domini ማለት የጌታ ዓመት) ወይም AD ተብሏል። አሁንም ሌላ ዘመናዊ ቄንጥ CE (ከእንግሊዝኛኮመን ኤራ ወይም «የጋራ ዘመን») ብዙ ጊዜ ይታያል። የዚህ የዓመት አቆጣጠር ከኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር «ዓመተ ምኅረት» በ፯ ወይም ፰ አመቶች ይለያል።