ኦሮሚያ ክልል

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
ኦሮሚያ ክልል
ክልል
Oromia in Ethiopia.svg
የኦሮሚያ ክልልን በቀይ የሚያሳይ የኢትዮጵያ ካርታ
Flag of the Oromia Region.svg
አገር ኢትዮጵያ
ርዕሰ ከተማ አዲስ አበባ
የቦታ ስፋት
   • አጠቃላይ 254,538[1]
የሕዝብ ብዛት
   • አጠቃላይ 31,294,992[1]

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትልቁን የሀገሪቱን የቆዳ ስፋት የያዘ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅትም በ12 አሰተዳደራዊ ዞኖችና በ180 ወረዳዎች የተዋቀረ ነው፡፡ ከነዚህ 12 ዞኖች ውስጥ፣ የባሌና ቦረና ዞኖች 45.7 ከመቶ የሚሆነውን የክልሉን መሬት ሲይዙ በህዝብ ሰፈራ ረገድ ግን የክልሉን 14 ከመቶ ብቻ ይኖርባቸዋል፡፡ የኦሮሚያ ምክር ቤት የክልሉ አስተዳደር ከፍተኛው መዋቅር ነው፡፡

ርዕሰ ከተማ

አዲስ አበባ (ፊንፊኔ) የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ ከተማ ነች፡፡

የስፍራው አቀማመጥ

የኦሮሚያ ክልል በሰሜን ከአፋር፣ ከአማራ እና ቤኒሻንጉል-ጉምዝ ክልሎች፣ በምስራቅ ከሶማሌ ክልል፣ በምእራብ ከሱዳን ሪፐብሊክ፣ ከቤኒሻንጉል-ጉምዝ ክልልና ከደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል፣ እንዲሁም በደቡብ ከኬንያና ከጋምቤላ ክልል ጋር ይዋሰናል፡፡

የቆዳ ስፋት

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት 353‚690 ስኩ.ኪ.ሜ የሚገመት የቆዳ ስፋት ይሸፍናል፡፡ ይህም የሀገሪቱን 32 ከመቶ የቆዳ ስፋት ይይዛል፡፡

ስነ-ህዝብ

በ1994 በተገኘው የህዝብ ቆጠራ መሰረት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የህዝብ ብዛት 18,732,525 ሲሆን ከዚህም ውስጥ 9,371,228 ወንዶች እና 9,361,297 ሴቶች ናቸው፡፡ 89.5 ከመቶ የሚሆነው በገጠራማው የክልሉ ቦታዎች ይኖራል፡፡ በሀይማኖት ረገድም 44.3 ከመቶ የእስልምና፣ 41.3 ከመቶ የኦርቶዶክስ ክርስትያን፣ 8.6 ከመቶ የፕሮቴስታንት የተቀረው 4.2 ከመቶ የባህላዊ እምነት ተከታይ ነው፡፡ በክልሉ የከተማ አካባቢዎች ግን 67.8 ከመቶ የኦርቶዶክስ ክርስትያን፣ 24.0 ከመቶ የእስልምና እንዲሁም 7 ከመቶ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ነው፡፡

በብሄር ስብጥር አኳያም 85 ከመቶ የኦሮሞ፣ 9.1 ከመቶ የአማራ፣ 1.3 ከመቶ የጉራጌ፣ የተቀረው 4.6 ከመቶ የሌሎች ብሄረሰቦች ይኖራሉ፡፡

በአሁኑ ጊዜ በላቲን ፊደላት የተቀረፀው የኦሮሚኛ ቋንቋ የክልሉ የስራ ቋንቋ ሲሆን 85.5 ከመቶ በክልሉ ይነገራል፣ አማርኛ 11 ከመቶ፣ ጉራጊኛ 0.98 ከመቶ፣ ጌዴኦኛ 0.98 ከመቶ እንዲሁም ትግርኛ 0.25 ከመቶ በክልሉ የሚነገሩ ቋንቋዎች ናቸው፡፡

ዋነኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትከሚገኘው ህዝብ 90 ከመቶየሚሆነው ህዝብ ኑሮውን የግብርና ስራ ላይ ያደረገ ነው፡፡ በክልሉ በቆሎ፣ ገብስ፣ ጤፍ፣ ስንዴ፣ ሽንብራ እና ባቄላ እንዲሁም የተለያዩ የቅባት እህሎች በከፍተኛ ደረጃ የሚመረቱ ሰብሎች ናቸው፡፡ ቡና ለገበያ የሚቀርብ ምርት ነው፡፡ ክልሉ 51.2 ከመቶ የሚሆነውን የሰብል ምርት ከዚህም ውስጥ 45.1 ከመቶ የሚሆነው ጊዜያዊ ሰብሎች፣ እንዲሁም 44 ከመቶ የሚሆነውን የቁም ከብት ሀብት ለሀገሪቱ ያበረክታል፡፡

ኢትዮጵያ

ታሪካዊ ቦታዎች - አክሱም | ላሊበላ | ጎንደር | ነጋሽ | ሐረር | ደብረ-ዳሞ | አዲስ አበባ
አስተዳደራዊ ክልሎች - ትግራይ | አፋር | አማራ | ኦሮሚያ | ሶማሌ | ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል | ደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች | ጋምቤላ | ሐረሪ | አዲስ አበባ | ድሬዳዋ
ቋንቋዎች - አማርኛ | ግዕዝ | ኦሮምኛ | ትግርኛ | ጉራጊኛ | ሶማሊኛ | አፋርኛ | ሲዳምኛ | ሃዲያኛ | ከምባትኛ | ወላይትኛ | ጋሞኛ | ከፋኛ | ሃመርኛ | ስልጢኛ | ሀደሪኛ
መልክዓ-ምድር - አባይ | አዋሽ | ራስ-ዳሽን | ሶፍ-ዑመር | ጣና | ደንከል | ላንጋኖ | አቢያታ | ሻላ
ከተሞች - የኢትዮጵያ ከተሞች

ማመዛገቢያዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ "፳፻፬ ዓ.ም. ብሔራዊ ስታቲስቲክስ". ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ. በሰኔ ፳፪ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. የተወሰደ.