ኦጋም ጽሕፈት
Appearance
(ከኦጋም የተዛወረ)
ኦጋም ጽሕፈት ለጥንታዊ አይርላንድኛ ቋንቋ የተጠቀመ አጻጻፍ ነበረ። በአይርላንድና በታላቅ ብሪታንያ ምዕራብ 400 ያህል በኦጋም ፊደል የተጻፉ ቅርጾች ተገኝተዋል። እነዚህ በብዛት ከ300 ዓ.ም. እስከ 1000 ዓ.ም. ድረስ በድንጋይ ወይም በእንጨት የተቀረጹ ናቸው። እንዴት እንደ ተለማ የሚገልጹ ሀሣቦች ብዙ ናቸው። በአይርላንድ ትውፊቶች ዘንድ በፌኒየስ ፋርሳ ወይም በኦግማ በጥንት ከባቢሎን ግንብ ቀጥሎ ተፈጠረ።
ፊደሉ ለመቅረጫ በጣም ተስማሚ ነው። ለእያንዳንዱ ተናባቢ ድምጽ ከ1 እስከ 5 ምልክቶች ወይም ከመካከለኛው መስመር ግራ፣ ወይም ቀኝ፣ ወይም ሁለቱም አሉ። ሁለቱም ሲሆን ምልክቶች ካላንጋደዱ ግን አናባቢዎች ያመልከታሉ። ተራ ያልሆነ አናባቢ በልዩ ምልክትም ይጠቆማል።
በአንዳንድ ደራሲ እንደ ባሪ ፌል ዘንድ፣ ይህ አይነት አጻጻፍ ደግሞ በእስጳንያ፣ በፖርቱጋል እንዲሁም በስሜን አሜሪካ (ለምሳሌ በትርኪ ተራራ) በሰፊ ተገኝቷል።