ትርኪ ተራራ
Appearance
}}
ትርኪ ተራራ | |
---|---|
ከፍታ | 245 ሜትር |
ሀገር ወይም ክልል | ቱልሳ፣ ኦክላሆማ ክፍላገር፣ አሜሪካ }| |
ቀላሉ መውጫ |
ትርኪ ተራራ በቱልሳ አካባቢ ኦክላሆማ ክፍላገር አሜሪካ ውስጥ ከአርካንሳው ወንዝ አጠገብ የሚገኝ ሲሆን እንዲያውም ተራራ ሳይሆን ትልቅ ኮረብታ ነው። በዚያ ላይ በተገኙት ድንጋዮች ላይ ያሉት ምልክቶች 'የጥንታዊ አሜሪካ መዝገቦች' ተብለዋል። በአንድ ዋሻ ውስጥ የተቀረጹት ስዕሎችና ምልክቶች ከውቅያኖስ ማዶ የመጡት መርከበኞች ሥራ መሆናቸውን አንዳንድ ምሁር ያምናል።
በዋሻው የሚታይ አንዱ ምልክት የላቲን አልፋቤት ፊደላት «PIA» ይመስላል። ከዚህ በላይ አንዳንድ መስመር ሊታይ ይችላል። አወዛጋቢው ምሁር ባሪ ፌል ይህን «PIA» የሚለውን ቃል ከ«A»-ኡ ቅርጽ የተነሣ እጅግ ጥንታዊ መሆኑን ገመተ። በሱ አስተሳሰብ በከነዓን ቋንቋ የተጻፈው 'ፓያ' ወይም 'ነጭ' ለማለት ነው። መስመሮቹ ደግሞ የኦጋም ፊደል መስለውት በጎይደሊክ ቋንቋ 'ጒን' ወይም 'ነጭ' እንደሚል ያምናል። በሁለት ቋንቋዎች የተጻፈ ቃል ማለቱ ይሆናል።
ይህ ሥፍራ ልክ በጋዲር ('የሄራክሌስ ዓምዶች' ወይም የዛሬው ካዲዝ) ኬክሮስ ላይ (36 N) ይገኛል። በመጽሐፈ ኩፋሌ መሠረት ከጋዲር ወደ ምዕራብ የሚሄድ መስመር የሞሳሕ ያፌት ርስት ከከነዓን ካም ርስት ይለያል።
- በኦክላሆማ ውስጥ የሚገኙት ምልክቶች ከነትርኪ ተራራ Archived ሴፕቴምበር 8, 2006 at the Wayback Machine(እንግሊዝኛ)
- ስለ ትርኪ ተራራ ጽሕፈቶች Archived ጁን 22, 2007 at the Wayback Machine (እንግሊዝኛ)