ከመሶብዎ አይጡ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ከመሶብዎ አይጡ

(40)ሰው መቼም ወዶም ይሁን ፈርቶ አለቃን ይጋብዛቸዋል። አንድ ቀን ሊጋበዙ ወደ አንዱ ቤት ጎራ ብለው እንደተቀመጡ ጋባዥዋ ሴት እንጀራ ለማቅረብ መሶቡን ከፈት ስታደርገው ትንሽ አይጥ ዘላ ትወጣና ትሰወራለች። አለቃም ይህችን ጠንቀኛ አይጥ አይተዋት እንዳላዩ ጸጥ ብለዋል። ርቧቸው ስለነበረ ከራሳቸው ጋር እየታገሉ እስኪበቃቸው ድረስ ይበላሉ። ከዚያም በመጨረሻ ማእድ ሲነሳ መመረቅ የተለመደ በመሆኑ እንዲህ ብለው ይመርቃሉ ;- በላነው ጠጣነው ከእንጀራ ከወጡ እ /ር ይስጥልኝ ከመሶብዎ አይጡ።