ከአልጋ ላይ ወድቄ ነው

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ከአልጋ ላይ ወድቄ ነው

(35) አለቃ አንድ ቀን መንገድ መሽቶባቸው አንዲት ሴትዮ ቤት እንድታሳድራቸው ለምነው ቤት ለእንግዳ ብላ አስገባቻቸው። አለቃ ያው እንደሚተረከው ቅንዝራም ቢጤ ናቸው። እራት በልተው ከጨረሱ በኋላ በሉ እኔ መደብ ላይ እርሶ መሬት ላይ ተኙ ብላቸው ተኙ። ከዚያ ጨለማን ተገን በማድረግ ሴትየዋ መደብ ላይ ዘፍ ብላው መዳሰስ ይጀምራሉ። ሴትየዋም በድንጋጤ ነቅታ እንዴ ምን እየሰሩ ነው ስትላቸው ከአልጋ ላይ ወድቄ ነው አሏት። እንዴት መሬት ተኝተው ስትላቸው እኔንስ የገረመኝ እሱ አይደል አሏት ይባላል።