ኩኩ ሰብስቤ
ኩኩ የኢትዮጵያ ታዋቂ ዘፋኝ ስትሆን ብዙ ዘመናዊ የሙዚቃ ስራወችን በማቅረብና የቁንጅና ውድድር በማሸነፍ ትታወቃለች።
ለስለስ ባሉ ዜማዎቿ ትታወቃለች :: በልጅነቷ የወንድ የሴት ሳትል ከእሷ ድምፅ ጋር የሚሄዱትን ሙዚቃዎች ተጫውታለች፡፡ የእነ ሙሉቀን መለሰ ፣ ጌታቸው ነሳ ፣ ሽሽግ ቸኮል ፣ እታገኘሁ ሀይሌ እና ብዙነሽ በቀለን እና ሌሎችንም ሰርታለች። በጊዜው ቆየት ያሉትን የእንግሊዘኛ ሙዚቃዎች በማድመጥ አስከማንጎራነርም ደርሳ ነበር፡፡ ተወዳጇ ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ፡
ገና ከልጅነቷ ጀምሮ ት/ቤት ውስጥ በማንጎራጎር ነው ሙዚቃን የጀመረችው፡፡ በጊዜውም ሙሉቀንን ታደንቀው ስለነበረ ከአባቷ ከደጃዝማች ሰብስቤ ሽብሩ እየወሰደች (የእሳቸውን እና የሌሎችም) የግጥም ስራዎች ትሰጠው ነበር፡፡ ሙሉቀን መለሰም "ናኑ ናኑ ነይ" የተሰኘ አልበሙን ሲያወጣ በጊዜው የግጥም ደራሲዬ ኩኩ ሰብስቤ ናት እስከ
ማለትም ደርሶ ነበር፡፡
ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ የመጀመረያ የመድረክ ስራዋን ያቀረበችው ከአይቤክስ እና ዋልያስ ባንድ ጋር በመሆን በሂልተን ሆቴል በተዘጋጀ የተማሪዎች ፓርቲ ላይ ነበር፡፡ በዚህ መድረክ ላይ የታጨችው ድምፃዊት ኩኩ ራስ ሆቴል በ300ብር ተቀጥራ ከመሀሙድ አህመድ ጋር በአይቤክስ ባንድ አጃቢነት በሳምንት ሁለት ቀን ትጫወት ነበር፡፡ በኋላ ላይም ወደ ሂልተን ሆቴል በመዛወር በ6ዐዐብር በየቀኑ ከዋልያስ ባንድ ጋር ትሰራ ነበር፡፡ በጊዮን ሆቴል ከሮሃ ባንድ ጋርም ትጫወት ነበር። በዚሁ ባንድ አጃቢነትም ከአለማየሁ እሸቴ ጋር “እንግዳዬ ነሽ" የተሰኘ የመጀመሪያ ስራዋን ለህዝብ አድርሳለች፡፡ ቀስ በቀስም ከሮሃ ባንድ ጋር ሶስት ያህል አልበሞችን አውጥታለች።
ከተለያዩ አንጋፋ ድምፃውያን ጋር በቅብብሎሽ የሰራቻቸውም በሮሃ ባንድ የተቀናበሩ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ከአይቤክስ ፣ ዋልያስ ፣ ሮሃ ፣ ኢትዮ ስታር እና ኤክስፕረስ ባንዶች ጋር በተለያዩ ጊዜያት ሰርታለች፡፡ በተለይ በትዝታ ስራዎቿ የምትታወቀው ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ እስካሁን ስምንት ያህል አልበሞችን ሰርታለች፡፡ የመጨረሻ አልበሟ "ቻለኩበት" የተሰኘው ሲሆን በቀጣይም ሌላ አልበም ለመስራት እየተዘጋጀች ነው፡፡ በርከት ያሉ ነጠላ ዜማዎች ያሏት ሲሆን በቅርቡም "ሰበቤ" የተሰኘ ነጠላ ዜማዋን ለአድናቂዎቿ ጀባ ብላለች፡፡ አሳካሁን ባላት የካበተ ልምድ በሀገር ውስጥ እና በውጪ ኮንሰርቶቿን አቅርባለች፡፡ በጅቡቲ ጀምራ ሰነዓ፣ አቡዳቢ ፣ የመን ፣ ዱባይ ፣ አሜሪካ (በተለያዩ ከተሞች) እና በታላላቅ የአውሮፓ ከተሞች በመዘዋወር ሙዚቃዎቿን ለአድናቂዎቿ ተጫውታለች።
- ፲፱፻፺፰ ዓ.ም. ትዝታ
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |