Jump to content

ኪሩቤል

ከውክፔዲያ

ኪሩቤል አራት ናቸው አንደኛው ገጽ ብእሲ ይባላል ይህ የሰው መልክ ያለው ሲሆን ለሰው ልጆች ሁሉ እግዚአብሔር ኃጢአታቸውን ይቅር እንዲላቸው እና በቸርነቱ እንዲጠብቃቸው ያለ

እድሜያቸው እንዳይውስዳቸው የሚጸልይ መልአክ ነው

ሁለተኛው ገጸ አንበሳ ይባላል የአንበሳ መልክ ያለው መልአክ ሲሆን አንበሳ የአራዊት ንጉሥ እንደሆነ ሁሉ ለአንበሳ እና ለአራዊቱ የሚጸልይ መልአክ ነው ሶስተኛው ገጸ ላህም ይባላል የላም መልክ ያለው ሲሆን እንስሳት እርስ በርስ ተነካክሰው እንዳይጠፉ የሚጸልይ መልአክ ነው አራተኛው ገጸ ንስር ይባላል ንስር የአእዋፋት ንጉሥ ሲሆን በክንፍ በሰማይ እየበረረ ከላይ ወደታች ሲመለክት በምድር ላይ ያሉትን ረቂቃን ማየት እንደሚችል ሁሉ ለአእዋፋት የሚጸልይ መልአክ ነው