ካርል አዶልፍ አጋርድ
ካርል አዶልፍ አጋርድ (ጥር 23 ቀን 1785 በባስታድ፣ ስዊድን - ጥር 28 ቀን 1859 በካርልስታድ ) ስዊድናዊ የእጽዋት ተመራማሪ ሲሆን በዋቅላሚዎች ላይ በትኩረት የሰራ እና በመጨረሻም የካርልስታድ ቢሾፕ ሆኖ ተሾመ።
እ.ኤ.አ. በ 1807 በሉንድ ዩኒቨርሲቲ የሂሳብ መምህር እንዲሆን ተሹሞ ነበር፣ በ 1812 የእጽዋት እና የተፈጥሮ ሳይንስ ፕሮፌሰር ሆኖ ተሾመ ፣ እናም በ 1817የስዊድን ሮያል ሳይንስ አካዳሚ አባል ሆኖ ተመረጠ።
እ.ኤ.አ. በ 1816 ቄስ ሆኖ ተሹሟል ፣ ሁለት አጥቢያዎችን እንደ ቅድመሁኔታ ተቀበለ እናም ከ 1817 ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት በስዊድን ፓርላማ የቄስ ክፍል ተወካይ ነበር። እ.ኤ.አ. በ1819-1820 የሉንድ ዩኒቨርሲቲ ሬክተስ ማግኒፊከስ ነበር።በ1835 የካርልስታድ ቢሾፕ ሆኖ ተሹሞ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ቆየ[1]። ካርል አዶልፍ አጋርድ የጃኮብ ጆርጅ አጋርድ አባት ፣ እንዲሁም የእጽዋት ተመራማሪ ነበር።[2]
ዘ ክላስስ ፕላንታረም[3] መደቦቹ እና አስተኔዎቹ የተመደቡባቸው ዘጠኝ ዋና ክፍሎች አሉት ። እነዚህም በመደብ ቁጥር ነበሩ።
- አኮቲሌዶኔ 1–3 (ዋቅላሚዎች፣ የድንጋይ ሽበቶች፣ ፈንገሶች)
- ሱዶኮቲሌዶኔ 4–7 (ሙስቾኢዲዬ፣ ትራዲዲሜ፣ ፊሊሰስ፣ ኤኩዊሴታሲዬ)
- ክሪፕቶኮቲሌዶኔ 8–12 (ማክሮፖዴ፣ ስፓዲሲኔ፣ ግሉሚፍሎሬ፣ ሊሊፍሎራ፣ ጂናንዳሬ)
- ፋኔሮኮቲሌዶኔ ኢንኮምፕሊቴ 13–16 (ሚክራንቴ፣ ኦሌራሲዬ፣ ኤፒክላሚዲዬ፣ ኮሉምናንቲሬ)
- ፋኔሮኮቲሌዶኔ ኮምፕሊቴ፣ ሃይፖጋይኔ፣ ሞኖፔታሌ17 ( ቱቢፍሎሬ)
- ፋኔሮኮቲሌዶኔ ኮምፕሊቴ፣ ሃይፖጋይኔ፣ ፖሊፔታሌ18-22 (ሴንትሪፖሬ፣ ብሬቪስቲሌ፣ ፖሊቻርፔሌ፣ ቫልቪስፖሬ፣ ኮሉምኒስፌሬ)
- ፋኔሮኮቲሌዶኔ ኮምፕሊቴ፣ ዲሲጋይኔ፣ ሞኖፐታሌ 23 (ቴትራስፕርሜ)
- ፋኔሮኮቲሌዶኔ ኮምፕሊቴ፣ ዲሲጋይኔ፣ ፖሊፐታሌ፣24–26 (ጋይኖባዛሲዬ፣ ትሪሂሊቴ፣ ሃይፖዲቻርፔ)
- ፋኔሮኮቲሌዶኔ ኮምፕሊቴ፣ ፖሪጋይኔ27–33 (ሰብአግሪጋቴ፣ አሪዲፎሊዬ፣ ሰኩለንቴ፣ ካሊካንቴሜ፣ ፔፖኒፌሬ፣ ኢኮሳንድሬ፣ ሌጉሚኖሴ)
ከዚያም እያንዳንዱ መደብ በርካታ ክፍለመደቦችን (አስተኔዎችን) ይይዛል። ለምሳሌ፣ ሊሊፍሎሬ 11 ክፍለመደቦችን ይዟል፤
- ሊሊፍሎሬ
- 43 አስፓራጂዬ
- 44 አስፎዲሊዬ
- 45 ኮሮናሪዬ[lower-alpha 1]
- 46 ቬራትሪዬ
- 47 ኮሜሊኒዬ
- 48 ፖንቲዴሪዬ
- 49 ዲዮስኮሪኔ
- 50 ሄሞዶሪዬ
- 51 አይሪዲዬ
- 52 ናርሲሲዬ
- 53 ብሮሚሊያሲዬ
ለፖለቲካዊ ኤኮኖሚ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ነበር፣ እናም እንደ "ቀዳሚ ሊበራል" "በስዊድን ውስጥ የትምህርት ደረጃዎችን ማሻሻል ተሳክቶለታል" [3]በተጨማሪም በሥነ መለኮት እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ጽፏል፣ ነገር ግን ዝናው በዋናነት በእጽዋት ሥራዎቹ ላይ ያተኮረ ነው።በተለይም ሲስቴማ አልጋረም፣ ስፒሽየስ አልጋረም፣ ሪቴ ኮግኒቴ፣ ክላስስ ፕላንታረም ኦን ባዮሎጂካል ክላሲፊኬሽን[4] እና ኢኮኒስ አልጋረም (1824፣ 1820–28 እና1828-35)በተሰኙት ስራዎቹ ይታወቃል።የእጽዋት መጽሃፉ ትልቁ ክፍል (2 ጥራዝ፣ ማልሞ፣ 1829–32) ወደ ጀርመንኛ ተተርጉሟል።
- Algarum decas prima [-quarta] /auctore Carolo Ad. Agardh
- Dispositio algarum Sueciae /cuctore Carolo Adolfo Agardh
- Caroli A. Agardh Synopsis algarum Scandinaviae : adjecta dispositione universali algarum
- Adnotationes botanicae (with Swartz, Olof, Sprengel, Kurt Polycarp Joachim, and Wikström, Joh. Em)
- ^ Eriksson, Gunnar (1970). "Agardh, Carl Adolph". Dictionary of Scientific Biography. Vol. 1. New York: Charles Scribner's Sons. pp. 69–70. ISBN 0-684-10114
- ^ Ripley, George; Dana, Charles A., eds. (1879). "Agardh, Karl Adolf" . The American Cyclopædia.
- ^ Gilman, D. C.; Peck, H. T.; Colby, F. M., eds. (1905). "Karl Adolph Agardh". New International Encyclopedia (1st ed.). New York: Dodd, Mead.
- ^ Agardh 1825