ካንጋሮ

ከውክፔዲያ
ወንድ ካንጋሮች ብዙ ጊዜ ቡጢ ያደርጋሉ።

ካንጋሮች በአንድ ሃገር ብቻ ነው የሚገኙት፤ እሱም ምድረ አውስትራሊያ ናት። ለሃገሪቱም እንደ ምልክት እና ብሄራዊ ገፅታ (አርማ) ተደርገው ይታያሉ።

የካንጋሮዎች መንጋ «ሞብ» ይባላል፤ መንጋውም 10 እና ከአስር በላይ ቁጥር ያላቸውን ካንጋሮች ይይዛል።

ትልቅ ወንድ ካንጋሮ 2 ሜትር ሲረዝም 90 ኪ.ግ ይመዝናል።

ሴቱም ከወንዱ በተቀራረበ መልኩ ትመዝናለች ትከብዳለች።

የካንጋሮችን ፆታ የሚለየው ሴቱ ደረቷ ላይ ባለው ከረጢት መሰል ነገር እና በመራቢያ አካሎቻቸው ነው።

ካንጋሮዎች በሚወለዱ ጊዜ ቁመታቸው 1 ኢንች፣ ክብደታቸውም 1 ግራም ብቻ ነው። ልክ እንደተወለዱም ያለማንም እርዳት (አጋዥ) በደመነፍስ በመንሸራተት እናታቸው ደረት ላይ ወዳለው ከረጢት ይገባሉ።

ከዛም ለ7 ወር በእናታቸው ሆደ ከረጢት ዉስጥ ቆይተው አድገው ይወጣሉ።

ካንጋሮዎች በፍጥነት በሚሮጡበት ጊዜ ከ60-70 km ይጓዛሉ።

ካንጋሮዎች ሚዛናቸውን የሚጠብቁት በጭራቸው ነው።

የካንጋሮ ስጋ በዉስጡ 2% ዝቅተኛ ቅባት የያዘ በመሆኑ እና በዉስጡ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን በመያዙ ለጤና ጠቃሚ ነው።

አዉስትራሊያም ለተለያዩ የአለም ሃገራት የካንጋሮ ስጋን በመላክ ከፍተኛ የሆነ የገቢ ምንጭ ሆኖታል።

ስም[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

«ካንጋሮ» የሚለው ቃል በእንግሊዝኛ (Kangaroo /ካንጋሩ/) በኩል፣ የተወሰደው ከአውስትራልያ ኗሪ ቋንቋ ጉጉ ይምጥርኛ ቃል «ካንጉሩ /ጋንጉሩ» ነበር። ይህም ማለት «ምሥራቅ ግራጫ ካንጋሮ» ነው። (ለሌሎቹ ዝርዮች ግን በጉጉ ይምጥርኛ ልዩ ልዩ ስሞች አሉ።)

ዝርዮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አራት ካንጋሮ ዝርዮች በአውስትራልያ አሉ፦

እንዲሁም በአውስትራልያና በኒው ጊኒ ላይ ከካንጋሮ አነስተኛ የሆኑት በርካታ ሌሎች ተመሳሳይ እንስሶች አሉ፣ እነዚህ ዋላቢዋላሩ፣ እና የዛፍ ካንጋሮ ናቸው። በተጨማሪ የተዘመደው አይጥ ካንጋሮ በአውስትራልያ አለ። ከዚህም ሌላ በስሜን አሜሪካዘራይጥ ክፍለመደብ ውስጥ ካንጋሮ አይጥ የተባለ ፍጡር አለ።