ካይዘን

ከውክፔዲያ

ካይዘን (ጃፓንኛ፦ 改善 «ማሻሻል» ማለት ነው) የአመራር ፍልስፍና ነው። ከጦርነቱ በኋላ በጃፓን ድርጅቶች ተለማ። በአንዳንድ ኢንዱስትሪ በተለይም በአንዳንድ መኪና ፋብሪኮች (ቶዮታ ድርጅት) በተግባር ውሏል።

የካይዘን ፍልስፍና ዘዴ በአጭሩ «ማቀድ -> ማድረግ -> ማመልከት -> መገሰብ/ማስተካከል» ይባላል። በተጨማሪ ማናቸውም ዕንቅፋት በደረሰ ጊዜ የሥሩን ጠንቅ ለማወቅ አምስት ጊዜ «ለምን» መጠይቅን ያስተምራል። (እያንዳንዱ ምክንያት ላይኛ ምክንያት እንዳለው በማሠብ)። እንዲህ ሲደረግ አንድ የሚታወስ መርኅ «የሚጎደለው ሂደቱ እንጂ ሰዎቹ አይደሉም» ነው ይባላል።

የ«ካይዘን» ትርጉም ከጃፓንኛ እንዲያውም «ማሻሻል» ሲሆን፣ ብዙ ጊዜ ፅንሰ ሀሣቡ እንደ «ምንጊዜም ማሻሻል» ይተረጎማል።