ክራኑስ ራዜኑስ
Appearance
ክራኑስ ራዜኑስ በጣልያናዊ መኖኩሴ አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ ጽሑፍ ዘንድ (1490 ዓ.ም. የታተመ)፣ በጣልያን ሀገር የነገሠ ንጉሥ ነበር። የያኑስ ልጅ ይባላል። ሳባትዩስ ሳጋ ከሞተ በኋላ (2219 ዓክልበ. ግድም) ያኑስ ክራኑስን ከቲቤር ወንዝ ደቡብ ያለው ክፍል ገዥ ሾመው። ከ8 አመት በኋላ (2211 ዓክልበ. ግድም) ያኑስ እራሱ ሲሞት ክራኑስ የስሜን ጣልያ («ራዜና») ንጉሥ ሆኖ ተከተለው፤ የክራኑስም ልጅ አውሩኑስ የደቡብ ክፍል ገዥ ሆነ። ክራኑስ 54 ዓመታት እስከ 2158 ዓክልበ. ግድም ድረስ ነገሠ፤ ከዚያ ልጁ አውሩኑስ የስሜን ክፍል ንጉሥ ሆነ።
ቀዳሚው ያኑስ |
የራዜና (ጣልያን) ንጉሥ 2211-2158 ዓክልበ. ግድም (አፈታሪክ) |
ተከታይ አውሩኑስ |