ክዋቻ

ከውክፔዲያ

ክዋቻዛምቢያ ሕጋዊ ገንዘብ ስም ነው። አንድ ክዋቻ መቶ እንግዊ ማለት ነው።

እስከ ፲፱፻፹፬ ዓ.ም. ድረስ የዛምቢያ የወረቀት ገንዘብ የፕሬዚደንት ኬነዝ ካውንዳን ምስል ያሳዩ ነበር። ከ፲፱፻፹፭ ዓ.ም. ጀምሮ ግን የካውንዳ ምስል በ "የአፍሪቃ አሳ አጥማጅ ንስር" ምስል ተተክቷል።

የስሙ ምንጭ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ክዋቻ የሚለው ቃል በንያንጅኛ እና በቤምባ ቋንቋዎች ንጋት ማለት ሲሆን "አዲስ የነጻነት ንጋት" የሚለውን የዛምቢያን ብሔራዊ መፈክር ያስተጋባል። "እንግዊ" ደግሞ በንያንጅኛ ብርሃን ወይም መብራት ማለት ነው።