ኮረንቲ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
ብዙ መብረቆች ባንድ ላይ ሲወድቁ
መብረቅ የሚሰራው ከኮረንቲ ነው

ኮረንቲ ወይም ኤሌክትሪክ የሚባለው በኮረንቲ አስተላላፊ ቁስ አካል ውስጥ የሚገኙ ኤሌክትሮኖች በኤሌክትሪካዊ ሙል ተሞልተው (ቻርጅ ተደርገው) ወይም በመግነጢሳዊ ኃይል ተገፍተው ካንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሲንቀሳቀሱ ነው። ኮረንቲ እንግዲህ በተለያዩ ክስተቶች ዘንድ የመገኘት ባህርይ አለው።በስታቲክ ኤሌክትሪሲቲ በመፋተግ፣በሙቀት ልዩነት፣ጨረራ፣ኬሚካላዊ አጸግብሮት፣ኬሚካላዊ ንትበት(ዲኬይ) ለምሳሌ ያልን እንደሆን በመብረቅ፣ ጸጉራችንን በሚዶ በማበጠር በሚነሳው ቋሚ ኮረንቲ(ዲሲ ከረንት) እና እንዲሁም በተለዋዋጭ ማግኔት ማእበል መስክ ውስጥ የሚያቋርጥ በኮረንቲ አስተላላፊ(ኮንዳክተር) አካል ውስጥ የሚፈጠር ተለዋዋጭ ኮረንቲ(ኤሲ ከረንት) ሊገኝ ይችላል። ኮረንቲ በሁለት ምድብ ይከፈላል። ይኽዉም በ እንግሊዝኛ አባባል ኦልተርኔት ከረንት ወይም ኤሲ በመባል ሲታወቅ ሁለተኛው ደግሞ ዳይሬክት ከረንት ወይም ዲሲ በመባል ይታወቃል። ኮረንቲ በሁለት ተቃራኒ አውታር(ፖል) የሚፈስ ከሆነ ኦልተርኔት ከረንት ወይም ኤሲ የሚባል ሲሆን ኮረንቲ በአንድ አውታር(ፖል) ብቻ የሚፈስ ከሆነ ዳይሬክት ከረንት ወይም ዲሲ በመባል ይታወቃል።

hasot