ወሎ

ከውክፔዲያ

ወሎ (Wollo) በሰሜን ምስራቅ የኢትዮጵያ ክፍል የሚገኝ ታሪካዊ አውራጃ እና ክፍለ ሀገር ሲሆን ዋና ከተማዋ ደሴ ነው። ከ1700ዓም በፊት ከፊል የወሎ አካል ስሙ አምሐራ የነበረ ሲሆን 17ኛው ክፍለ ዘመንኦሮሞ መስፋፋትን ተከትሎ በአከባቢዉ በፊት አምሐራ ተብሎ የሚጠራውን አካባቢ ጨምሮ ወሎ በሚባል ሰፊ ግዛት አካታች በሆነ ስያሜ እና ማንነት መጠራት ጀመረ ። ወሎ እንዳሁኑ በስፋት ከመዋሀዱ በፊት በቀድሞ ካርታዎች "አምሐራ" በሚል ስያሜ በሰሜን በሽሎ ወንዝ፣ በደቡብ ጃማ ወንዝ፣ በምእራብ አባይና በምስራቅ አፋር ያዋስኑት ነበር። የወሎ ድንበር በየዘመኑ የመስፋት እና የመጥበብ ሁኔታዎች የሚታይበት ሲሆን በአንዳንድ የታሪክ አጋጣሚዎች እስከ አሰብ ድረስ ይሰፋ ነበር፡፡ ከጣልያን ጦርነት ቀጥሎ በ1933 ዓ.ም. አዛቦላስታራያዋግ እና የጁ ይፋዊ የወሎ ግዛቶች ሆኑ። ወሎ እጅግ ሰፊ የሚባል ጠቅላይ ግዛት የነበረ ሲሆን በስፋቱም ከሀረርጌ፣ ከባሌ እና ከሲዳሞ በመቀጠል በአራተኛ ደረጃ ላይ የቀመጣል ስፋቱም 79,4002 ስኩየር ኪሎሜትር ነበር፡፡

1987 ዓ.ም. ኢህአዴግደርግን ስረአት በሀይል በመጣል አገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላ ባወጣው ሕገ መንግሥት መሠረት፣ ወሎ የሚባል ራስገዝ የአውራጃ አስተዳደር በማስቀረት ግዛቱን በአፋር ክልልትግራይ ክልል፣ እና አማራ ክልል እንዲከፈል ተደረገ። ከዚህ የወሎ ግዛት መበታተን ጀምሮ የወሎ መዲና የሆነችው ደሴ ብዙ የልማት ዝቅተት አጋጥሟታል፣ መንገዶቿ ፈራርሰዋል፣ ከተማዋም ከመቶ አመት በላይ ስም ያላት ብትሆንም አስርት አመታት እድሜ ባላቸው ከተሞች ተበልጣ በመታየቷ የወሎ ህዝብን አንገት ያስደፋ ጉዳይ እንደሆነ ዘልቋል። አንዳንድ ምሁራን የወሎን የቁልቁለት ጉዞ ከተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች ጋር ለማያያዝ ቢሞክሩም ሁሉንም የሚያሳምን አይመስልም። ከታሪክ አጋጣሚዎች በላይ የወሎ እና የደሴ ከተማ ስመ ገናናነትን ውሀ የቸለሰበት ጉዳይ ህዝቡ አንድ ሆኖ በወሎየነት መንፈስ አለመሰለፉና የራሱን ታሪክ ጠንቅቆ ባለመረዳቱ ነው ይባላል። ምንም እንኳ የወሎ ህዝብ ስመገናናነት እንደ ድሮው ባይሆንም አሁን ላይ ባለው የእርስበርስ መስተጋብር፣ ባህል፣ ወግ፣ የሀይማኖት መቻቻል እና የሀሳብ አሸናፊነት ትልቅ ልዕልና እንዳለው በማሳየት ላይ ይገኛል።

ወሎ የክርስትናና እስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ተከባብረውና ተዋደው በጋራ የሚኖሩበት የመቻቻል ተምሳሌት የሆኑ ህዝቦች መገኛ ድንቅ አካባቢ ነው።

ከሀይማኖቱ ውጭ ካለ ሌላ እምነት ተከታይ ህዝብ ጋር በሰላም በመኖርም ለአለም ምሳሌ የሆነ ህዝብ ነው። ወሎ እጅግ ውብ የሆኑ ልጃገረዶች መፍለቂያ ነው።

ዶ/ር ዶናልድ ሌቪን "የአሁኗን ኢትዮጵያ የሰሯት ወሎዎች ናቸው፣ ልታመሰግኗቸው ይገባል"ይላል፡፡