ወረኢሉ

ከውክፔዲያ
(ከወረይሉ የተዛወረ)
Jump to navigation Jump to search

ወረኢሉአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች አንዱ ነው። ከተማው የተቆረቆረው በአጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት ሲሆን የቆረቆሩትም ራሳቸው ንጉሱ እንደሆኑ ይነገራል። ለአድዋ ጦርነት የክተት አዋጅ በታወጀበት ወቅት ንጉሱ ሰራዊታቸውን የሰበሰቡት በዚህ ከተማ ነው። ከተማው ከደሴ 91 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገናል።