ወርቃማ ዋቅላሚዎች

ከውክፔዲያ
ዳይኖብራዮን ዳይቨርጀንስ
ወርቃማ ዋቅላሚዎች

ክራይሶፋይቶች ወይም በተለምዶ ወርቃማ ዋቅላሚዎች በመባል የሚታወቁት ማይክሮስኮፓዊ የሆኑ እና አብዛኛውን ጊዜ በቡኒ-ወርቃማ ቀለማቸው የሚለዩ የዋቅላሚ ቡድኖች ናቸው፡፡ ይህም የሆነው ፊውኮዛንቲን የተሰኘ ሀመልሚል(ቀለም) በአረንጓቀፋቸው ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ እና ይህ ሀመልሚል ክሎሮፊል-ኤ እና ክሎሮፊል-ሲን ሸፍኖ የሚታይ በመሆኑ ነው፡፡ ወደ 200 ገደማ የሚሆኑ ወገኖች እንዲሆም ወደ 1000 የሚሆኑ የወርቃማ ዋቅላሚ ዝርያዎች ሲኖሩ የሚገኙትም በዋናነት ጨው አልባ በሆኑ የውሃ አካላት ውስጥ ነው፡፡ የተወሰኑ ዝርያዎች ከፊል ጨዋማ በሆኑ እና ሙሉ ለሙሉ ጨዋማ በሆኑ የውሃ አካላት ውስጥ ይገኛሉ፡፡[1]

  1. ^ Edward G. Bellinger, David C. Sigee John Wiley & Sons, 2011 Freshwater Algae: Identification and Use as Bioindicators