ዊጉርኛ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ኡይጉርኛ (ئۇيغۇرچە‎ / Uyƣurqə / Уйғурчә) በቻይና የሚናገር የቱርኪክ ቋንቋዎች አባል ነው። እንደ ዘመዱ ዑዝበክኛ የተወለደው ከጫጋታይ ቱርክኛ ነበረ።

በምዕራብ ቻይና ኡይጉሮች የሚበዙበት ክልሎች ሰማያዊ ናቸው

በድሮ (700 ዓ.ም. ገደማ) የጥንታዊ ኡይጉርኛ ፊደልሶግዲያን ፊደል ተለውጦ ይጠቀም ነበር። ደግሞ የኡይጉር መንግሥት የኦርኮን ጽሕፈት ይጠቀም ነበር። ኡይጉርኛ በቻይና የተጻፈበት ጽሕፈት ከ10ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የአረብኛ ፊደል ሲሆን በ1961 ዓ.ም. የቻይና መንግሥት የላቲን ፊደልን አይነት አወጣለት። በ1975 ዓ.ም. ግን የአረብኛ ፊደል ተመለሰለት። በተጨማሪ በቀድሞው ሶቭየት ኅብረት ውስጥ የሚኖሩ ኡይጉሮች በቂርሎስ ፊደል አይነት ይጽፋሉ።

ምሳሌ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በአረብኛ ፊደል:ھەممە ئادەم زاتىدىنلا ئەركىن، ئىززەت-ھۆرمەت ۋە ھوقۇقتا بابباراۋەر بولۇپ تۇغۇلغان. ئۇلار ئەقىلغە ۋە ۋىجدانغا ئىگە ھەمدە بىر-بىرىگە قېرىنداشلىق مۇناسىۋىتىگە خاس روھ بىلەن مۇئامىلە قىلىشى كېرەك

በላቲን ፊደል (ከ1961 እስከ 1977 ይጠቀም ነበር): H̡əmmə adəm zatidinla ərkin, izzət-h̡ɵrmət wə hok̡uk̡ta babbarawər bolup tuƣulƣan. Ular ək̡ilƣə wə wijdanƣa igə h̡əmdə bir-birigə k̡erindaxlik̡ munasiwitigə hax roh bilən mu’amilə k̡ilixi kerək.

በቂርሎስ ፊደል (ከቻይና ውጭ ይጠቀማል)፦ Һәммә адәм затидинла әркин, иззәт-һөрмәт вә һоқуқта баббаравәр болуп туғулған. Улар әқилғә вә виджданға игә һәмдә бир-биригә қериндашлиқ мунасивитигә хаш рох билән му’амилә қилиши керәк.

በግዕዝ ፊደል፦ ሀመ አደም ዛቲዲንላ አርኪን፥ ኢዘት-ሄርመት ወ ሖቁቅታ ባባራወር ቦሉፕ ቱኁልኃን። ኡላር አቂልኅ ወ ዊጅዳንኃ ኢገ ሀምደ ቢር-ቢሪገ ቀሪንዳሽሊቅ ሙናሲዊቲገ ሓሽ ሮሕ ቢላን ሙአሚለ ቂሊሺ ከረክ።

ትርጉም፦ «የሰው ልጅ ሁሉ ሲወለድ ነጻና በክብርና በመብትም እኩልነት ያለው ነው። የተፈጥሮ የማስተዋልና ኅሊናው ስላለው አንዱ ሌላውን በወንድማማችነት መንፈስ መመልከት ይገባዋል።» (ከተመድ መብቶች ጽሑፍ)

የቱርክኛ ቅድመ-ታሪካዊ አመጣት ሷዴሽ ዝርዝር