ዋናውን ይዘው

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ዋናውን ይዘው

(28) አለቃ በቀልዳቸው በመወደድም ይሁን በመፈራት የሚፈልጉትን የማግኘት እድላቸው ሰፊ ነው ይባላል። በመሆኑም አንድ ለቤተመንግስት ሰዎች ቅርብ የሆኑ ታዋቂ እመቤት ቤት በእንግድነት ይገቡና በዚህም በዚያም ብለው በድብቅ ከእመቤቲቱ ጋር ወሲብ ይፈጽማሉ። ከዚያም ለካ ባልጠረጠሩበት መንገድ ሚስጥሩ ሾልኮ ቤተክርስቲያን ከባልደረቦቻቸው ጆሮ ገብቶ ባልደረቦቻቸውን አስቆጥቷቸዋል። አጅሬ ይህን ጉድ ሳይሰሙ እንደልማዳቸው ስራቸውን ሰርተው አድረው ጠዋት አገልግሎት ሊሰጡ ወደ ቤተክርስቲያን ሲሄዱ ቀሳውስቱ ተመካክረው ከሴት ጋር አድረው መጥተው ቤተክርስቲያናችንን ሊያረክሱብን አይገባቸውም ብለው ሰድበው ያብርሯቸዋል። አለቃም ባጋጠማቸው ነገር አዝነው ከቤተክርስቲያኑ ይወጡና ካጥር ውጪ ድንጋይ ላይ ቁጭ ብለው ዳዊታቸውን እየደገሙ ሳሉ እመቤቲቱ ፈረስ ላይ ቁጭ ብለው ከነአጃቢያቸው ይመጡና ከፈረሱ ወርደው ወደ ግቢ ያመራሉ። በዚህን ጊዜ አለቃ ብድግ ይሉና «በንጉስ አምላክ ይመለሱ! ወደ ውስጥ ሊያልፉ አይገባዎትም» ብለው ይጮሀሉ። ሰው ግራ ገብቶት «ምነው አለቃ ! ምን እያሉ ነው?» ሲል እሳቸውም ምንም የሌለው ምስኪን ካልተፈቀደለት እሳቸው ዋናውን ይዘው እንዴት ሊገቡ ይችላሉ?» በማለት ለሴትየዋ በሚገባ ዘዴ ተናግረው በማሳፈር መለሷቸው ይባላል።