Jump to content

ውክፔዲያ:ቀላል መማርያ/ገጽ 5

ከውክፔዲያ

ለማስታወስ የሚገባ ነጥቦች፦

  • ደግ ይሁኑ! ሌላ ሰው እርስዎ የማይወድዱትን ለውጥ ቢያደርግ፣ አብዛኛው ግዜ ለምንድነው ብለው ጨዋ መልእክት በመጣጥፉ ውይይት ገጽ ቢያስቀምጡ ጥሩ መመሪያ ነው።
  • የማያደላ አስተያየት ይጠብቁ። ይህ ማለት ለውጦች ሲያደርጉ የእርስዎን አስተያየት ብቻ ሳይሆን ስለ ሌላ ረገዶች ማሠብ ይመረጣል።
  • የሚጽፉትን ነገር ለመጽሐፈ ዕውቀት የሚገባ መሆኑን ይጠብቁ። መጣጥፎች ትንሽ ዝነኛነት ስላላቸው ጉዳዮች ቢሆኑ ይሻላል እንጂ ስለማይታወቅ ከንቱ ጉዳይ እንዳይሆኑ ሌሎቹ አዛጋጆች ገጽዎ እንዲደመስስ መጠየቅ ይችላሉ።
  • መብቱ የተጠበቀውን ሥራ መቅዳት አለመፈቀዱን ይገንዘቡ። የሰው ጽሑፍ ወይም ድረ ገጽ ቃል በቃል ከማዳገም ነገሩን በራስዎ ቃላት ለመግለጽ ቁም ነገር ነው።

አይዞት!

ከፍተኛ ጥረት ያለውን መጣጥፍ ለመጻፍ ብዙ ትጋት ይፈልጋል። ከሁሉ ይልቅ ለማስታወስ ግን ልትቀይሩት እንዳትፈሩ። ምንም ስህተት ሁሉ በቀላሉ የሚተካከል ነውና አይጨነቁ። ድምጻችሁን ጨምሩ።

ስታዘጋጁ ተጨማሪ እርዳታ ቢፈልጉ የማዘጋጀት እርዳታ እና የማዘጋጀት ዘዴ አሉ። መሰናከል ቢመጣብዎ ሌላ አዘጋጅ በውይይት ገጹ ላይ ይጠይቁ። ደግሞ መጋቢ (ሲሶፕ) መጠይቅ ይችላሉ። ሰው ምን ግዜ እኮምፒውተር ፊት አይኖርምና መልስ አሁኑን አይጠብቁ!


በቅተዋል!

[ኮድ አርም]

ጎበዝ! ብራቮ! ኮንግራ፣ ዊኪፔድያን ለመቀይር እናንተ አሁኑኑ ትችላላችሁ! ትዝ ለማለት እንደገና ለማጥናት ከወደዳችሁ በማንኛውም ሰዓት ወደዚሁ መማርያ መልሱ!

  • በመጽሐፉ ውስጥ በጠቅላላ ስለ አንዳችም ጉዳይ የሆነ ጽሑፍ ወዲያውኑ ለመፈለግ ካሰቡ፣ በኛ መደቦች ማውጫ ዛፍ ላይ መፈለግ እጅግ ጥሩ መነሻ ነው!