Jump to content

ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ሐምሌ 23

ከውክፔዲያ

፯፻፶፬ ዓ/ም የዛሬዋ የኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ ተመሠረተች።

፲፮፻፳፩ ዓ/ም ናፖሊ በተባለች የምዕራብ ኢጣልያ ከተማ በመሬት ነውጥ ፲ ሺህ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።

፲፱፻፳፪ ዓ/ም በኡራጓይ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር ዋንጫ ውድድር አስተናጋጇ ኡራጓይ ዋንጫውን ዋና ከተማዋ ሞንቴቪዲዮ ላይ አሸነፈች።

፲፱፻፵፰ ዓ/ም ፕሬዚደንት አይዘንሃወርአሜሪካ "የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት" (House of Representatives) እና "የእንደራሴዎች ሸንጎ" (Senate) በአንድነት ያጸደቁትን “በእግዚአብሔር እናምናለን” ("In God We Trust”) የሚለውን የአገሪቱን ብሔራዊ መፈክር ሕግ ፈረሙ።