ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ኅዳር 24
Appearance
- ፲፱፻፷ ዓ.ም. በደቡብ አፍሪቃ የቀዶ ጥገና ሐኪም ዶክቶር ክርስቲያን ባርናርድ የመጀመሪያው የሰው ልብ በ ’ቀዶ ጥገና’ ጥበብ ከሟቹ ‘ዴኒስ ዳርቫል’ ወደተቀባዩ የልብ በሽተኛ ‘ሌዊስ ዋሽካንስኪ’ አጠናቀቁ።
- ፲፱፻፷፱ ዓ.ም. በጃማይካ የ’ሬጌ’ ሙዚቃ ባላባት ቦብ ማርሌይ ላይ የገደላ ሙከራ ተደረገ። በሁለት ጥይቶች ቢመታም ማርሌይ ከሁለት ቀን በኋላ መድረክ ላይ ወጣ።
- ፲፱፻፸፬ ዓ.ም. ሕንድ አገር ውስጥ በቦፓል ከተማ ፥ የአሜሪካው ዩኒየን ካርባይድ ( Union Carbide) የኬሚካል ኩባንያ ውስጥ በተከሰተው አደጋ መርዛዊ ኬሚካል አየሩን በክሎት ሦስት ሺህ ስምንት መቶ ሰዎች ሲሞቱ እስከ ስድስት መቶ ሺህ ሰዎች በአደጋው ምክንያት ጤናቸው እንደተበላሸ ይገመታል።