ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/የካቲት 5
Appearance
- ፲፮፻፹፭ ዓ/ም - ንጉሡ አጼ ኢያሱ ከጳጳሱ አባ ሲኖዳ እና እጨጌ ዮሐንስ ጋር አክሱም እንዳሉ ሙራድ የተባለ ታላቅ ግብጻዊ ነጋዴ በሕንድ ውቅያኖስ መጥቶ ከሆላንድ ንጉሥ ያመጣውን ሰላምታ እና ደብዳቤ አቀረበ።
- ፲፯፻፰ ዓ/ም - ማክሰኞ ዕለት የአጼ ኢያሱ አድያም ሰገድ ልጅ ንጉሥ ዳዊት፣ አጼ ዳዊት አድባር ሰገድ ተብለው ዘውድ ጭነው ነገሡ።
- ፲፰፻፵፯ ዓ/ም - ደጃዝማች ካሳ ደረስጌ ማርያም ላይ አቡነ ሰላማ ቀብተዋቸው ዘውድ ጭነው ዓፄ ቴዎድሮስ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተባሉ።