Jump to content
ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ግንቦት 10
- ፲፱፻፲፪ ዓ/ም - የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ዳግማዊ ዮሐንስ-ጳውሎስ (የቀድሞው ካሮል ዮሴፍ ዎይቲላ) በፖላንድ ክራካው ከተማ በዚህ ዕለት ተወለዱ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ‘ፈገግተኛው ቡዳ’ በሚል መርሀ-ግብር ሕንድ የመጀመሪያዋን የኑክሊዬር ቦምብ በስኬታማነት አፈነዳች። በዚህ ተግባር በዓለም ስድስተኛዋ ባለ ኑክሊዬር ኃይል ሆነች።
- ፲፱፻፹፫ ዓ/ም - ሰሜናዊ ሶማሊያ ከዋናው አገር ተገንጥላ ነጻነቷን አወጀች። ሆኖም ይሄንን ድርጊት ማናቸውም የዓለም ቤተሰብ ዕውቀት አልሰጠውም።