ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ግንቦት 19

ከውክፔዲያ
  • ፲፱፻፳፪ ዓ/ም - በኒው ዮርክ ከተማ የ፩ሺ፵፮ ጫማ (፫መቶ ፲፱ ሜትር) ቁመት ያለው የ’ክራይዝለር’ ሕንፃ ተከፈተ።
  • ፲፱፻፶፮ ዓ/ም - የአዲሲቷ ሕንድ መስራችና ጠቅላይ ሚኒስትር ጃዋሃርላል ኔህሩ በተወለዱ በ፸፬ ዓመታቸው ድንገት አረፉ።
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኤርትራ ነጻነት ግንባር አባላት ጊንዳ ውስጥ በሉተራን ሚሲዮን ሆስፒታል ውስጥ የሚሠራ ዶክቶርን የመጥለፍ ሙከራ ሲያደርጉ አንዲት አስታማሚ (ነርስ) ተገደለች።
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የቴሌኮሙኒኬሽን ሠራተኞች በአድማ ሥራቸውን አቆሙ።