Jump to content

ውክፔዲያ:ክፍለ-ዊኪዎች

ከውክፔዲያ

የMediaWiki ሶፍትዌር የሚጠቅሙት ዊኪዎች ሁሉ 16 ክፍሎች ወይም ክፍለ-ዊኪዎች አሉዋቸው። ከነዚህም 15ቱ ልዩ 'ባዕድ መነሻ' (Prefix - ለምሳሌ 'ውክፔዲያ:_') ሲኖራቸው 16ኛው ምንም ባዕድ መነሻ ሳይኖረው ዋናው ክፍል (ለመጣጥፎቹ) ነው። ከ16ቱም አይነቶች ግማሹ ወይም 8ቱ የውይይት ክፍሎች ናቸው።

ክፍለ-ዊኪዎች

[ኮድ አርም]

1. ዋና ክፍል (Articles)

[ኮድ አርም]

ዋና ክፍል በአዚህ ዊኪ 'Articles' ይባላል (መጣጥፍ)። ይህ ክፍል ለመዝገበ ዕውቀት ጽሑፎች ብቻ ነው። ይህ ክፍል ምንም ባዕድ መነሻ የለውም። ስለዚህ፣ የያንዳንዱ ገጽ አርዕስት ከታች በተዘረዘሩት ባዕድ መነሻዎች በትክክል ባይጀመር፤ በአዚህ ክፍል በቀጥታ ይሆናል። በባዕዱ መነሻ የፊደል ግድፋትም ካለ፣ በስህተት በአዚህ ክፍል ይሆናል ማለት ነው። እንደዚህ ከሆነ ገጹን ወደሚገባው ክፍል መዛወር «ለማዛወር» የሚለውን በመጫን ቀላል ዘዴ ነው።

2. ውክፔዲያ:

[ኮድ አርም]

ይህ ክፍል ስለ ውክፔዲያ መርሀ ገብሩ መረጃ የሚሰጥ ገጽ ነው (ግብራዊ ገጽ)። ለምሳሌ ይኸው ገጽ እራሱ በ'ውክፔዲያ' ክፍለ-ዊኪ ይገኛል፤ አርእስቱ በ«ውክፔዲያ:» ይጀመራልና።

3. አባል: (User)

[ኮድ አርም]

ይህ ክፍል ለአባል (ተጠቃሚ፣ ብዕር ስም) የግል ገጾች ነው (ያባል መኖርያ ገጽ)። እነዚህ ገጾች በ«አባል:» መጀመር አለባቸው። ወደ ዊኪፔድያ ከገቡ፣ መኖርያ ገጽዎን ከላይኛ ጫፍ ብዕር ስምዎን በመጫን ይደርሳሉ። ይህ ገጽ የማይበቃዎ እንደሆነ፣ ተጨማሪ ገጾች መፍጠር ከስምዎ ቀጥሎ «/...(ምናምን)» በመጨመር ብቻ ነው።

4. ስዕል: (Image)

[ኮድ አርም]

ይህ ክፍል ለስዕል ወይም ለድምጽ መግለጫ ነው (ፋይል)። ይህ አይነት ገጽ ባእድ መነሻ «ስዕል:» ሲሆን በማንም ገጽ ላይ ስዕል እንዲታይ የዚህን ክፍል በማያያዝ ነው።

5. መልዕክት: (MediaWiki)

[ኮድ አርም]

ይህ ክፍል በመርሃ ግብሩ መልክ ላይ የሚታዩ ጽሑፎች (መልእክት) ነው። መልኩ በየጥቂቱ ከንግሊዝኛ ወደ አማርኛ ተተረጉሟል። ይህ ክፍል በ«መልዕክት:» ሲጀመር ከመጋቢዎቹ በቀር ለሌሎች ተጠቃሚዎች ግን ተቆልፈው ነበር።

6. መለጠፊያ: (Template)

[ኮድ አርም]

ይህ ክፍል ወደ ማንኛውም ገጽ መጨመር የሚችል ልዩ ጽሕፈት ነው (መለጠፊያ)። ክፍሉም «መለጠፊያ:» በሚለው ባእድ መነሻ መጀመር አለበት። በገጹ ላይ እንዲታይ {{(የመለጠፊያ ስም)}} በመጨመር በቀጥታ ይታያል።

7. መደብ: (Category)

[ኮድ አርም]

ይህ ክፍል (መደብ) ገጾች እንዲመደቡ የሚጠቅም ነው። ክፍሉ «መደብ:» በሚለው ባእድ መነሻ መጀመር አለበት። የገጹ ስም በሌላ ገጽ ሲጨመር ደግሞ የተጨመረበት ገጽ በዚያ መደብ ይታያል። መደቡ እራሱ የሌላ መደብ ንዑስ መደብ ሊሆን ይችላል። ይህ ዘዴ ስለ አንድ ጉዳይ የሆኑትን መጣጥፎች ለማግኘት በጣም ይጠቅማል። የአዚህ ሥራ እቅድ መደቦች ሁሉ በቀላል ለማመልከት፣ የመደቦች ዛፍ ይመለከቱ።

  • ማስታወሻ፦ ይህ አይነት ገጽ ሊዛወር አይችልም። የመደቡ እርእስት ለመቀየር በውስጡ ያለውን እያንዳንዱን ገጽ ወደ መደቡ አዲስ አርዕስት አንድ በአንድ መቀየር አለበት።

8. እርዳታ: (Help)

[ኮድ አርም]

ይህ ክፍል ልዩ ረድኤት የሚሰጡ ገጾች አሉት (እርዳታ ገጽ)። ባእዱ መነሻ «እርዳታ:» መሆን አለበት።

የውይይት (Talk) ክፍለ-ዊኪዎች

[ኮድ አርም]

ከላይ የተዘረዘሩት ክፍለ-ዊኪዎች እያንዳንዱ ደግሞ የራሱን ውይይት: ስፍራ አለው። የያንዳንዱ ክፍለ-ዊኪ ውይይት ክፍለ-ዊኪ የሚገኝ ለባዕዱ መነሻ «ውይይት:» በመጨመር ነው። ለምሳሌ የ«ውክፔዲያ» ውይይት ክፍል ባእድ መነሻ «ውክፔዲያ ውይይት:» ነው፤ የዋና ክፍልም ውይይት ክፍል ባዕድ መነሻ ዝም ብሎ «ውይይት:» ነው። እነዚህ ክፍሎች አብዛኛው ጊዜ ስለ ገጹ እራሱ ለመወያየት ነው። ይሁንና «አባል ውይይት:» የሚለው ክፍል ለአዚያ ተጠቃሚ መልእክት ለመተው ነው። በአዚህ ልዩ ክፍል (አባል ውይይት:) መልእክት ሲጨመር፣ «አዲስ መልእክት አለልዎት» የሚለው ብርቱካን ቀለም ሳጥን በአዚያው ተጠቃሚ መጋረጃ ጫፍ በቀጥታ ይታያል።