ውዳሴ ማርያም
Appearance
ውዳሴ ማርያም የሶርያው ቅዱስ ኤፍሬም የደረስውና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከጥንት ጀምሮ በጣም የታወቀና የተወደደ ጸሎት (የጸሎት መጽሐፍ) ነው። ይኸውም እመቤታችን ድንግል ማርያምን በብዙ ምሳሌ እየመሰለ የሚያወድስ፤ ስነ ጽሑፋዊ ውበት ያለው በመሆኑ ደግሞ ከጸሎትነቱም ባሻገር ጥልቅ ምስጢር ያለበት ትምህርት የሚሰጥ ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርአተ ትምህርት መሠረት ተማሪዎቹ በቃል ትምህርቱ ዘርፍ ከየዘወትር ጸሎት ቀጥለው በንባብና በዜማ ይህን ውዳሴ ማርያም የተባለውን የትምህርት ክፍል ይማሩታል።ይህን ትምህርት ከተማሩ በየእለቱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይደገማል።