ውዳሴ ማርያም ልደገም
Appearance
ውዳሴ ማርያም ልደገም
(21) አለቃ ገብረሀና የማይለመድ ለምደው ማታ ማታ ሰራተኛቸው ጋ ብቅ ሳይሉ አያድሩም ነበር። አንድ ቀን ሰራተኛቸው ጋ አምሽተው ቆይተው ቀስ ብለው ተደብቀው ገብተው ይተኛሉ። ትንሽ እንደቆዩ እንደገና ያምራቸውና ቀስ ብለው ምንም ሳያሰሙ እራቁታቸውን ሊሄዱ ሲነሱ ወ /ሮ ማዘንጊያ ነቄ አሉና «አንቱ ወዴት ኖት በዚህ በጭለማ» ብለው ወይዘሮ ማዘንጊያ ሲጠይቋቸው። «ቆዪ እስኪ አንዴ ውዳሴ ማርያም ደግሜ ልምጣ» አሉ። «ታዲያ ውዳሴ ማርያም እራቆት ተኩኖ ነው የሚደገም?» «ምን ላድርግ? እራቁቴን ሆኜ እንኳን ብትሰማኝ» ብለው እርፍ።